በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ ምርምር አምስት ሚሊየን ዶላር ተሰጠ


ፎቶ ፋይል፡-ዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ እና የማይክሮ ሶፍት መስራችና ባለቤት ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ
ፎቶ ፋይል፡-ዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ እና የማይክሮ ሶፍት መስራችና ባለቤት ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ኢንዲያና ግዛት ላፋዬት ከተማ የሚገኘው ፐርዱ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ በማሽላ ዘረመል ላይ ለሚያካሂዱት ጥናት የአምስት ሚሊየን ዶላር ስጦታ አገኙ።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ኢንዲያና ግዛት ላፋዬት ከተማ የሚገኘው ፐርዱ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ በማሽላ ዘረመል ላይ ለሚያካሂዱት ጥናት የአምስት ሚሊየን ዶላር ስጦታ አገኙ።

ወደ 135 ሚሊየን ብር ተኩል የሚገመተውን ስጦታ ለዶ/ር ገቢሳ ምርምር የሰጠው የቢልና ሜልንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ሲሆን ዶ/ር ገቢሳ ለሚያካሂዱት ምርምር እንዲህ ዓይነት እርዳታ ሲያገኙ ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽኑ ሁለተኛ መሆኑ ተዘግቧል።

እንዲህ ዓይነቱ ድጋፍ አሁን እየሠሩባቸው ካሉ ወሰኖችም አልፎ ለመሄድ የሚያስችል በመሆኑ ፋውንዴሽኑ በማደግ ላይ ባሉ ሃገሮች ውስጥ እያከናወናቸው ላሉ ፕሮግራሞች እጅግ ጠቃሚ እንደሚሆን ዶ/ር ገቢሳ ተናግረዋል።

ዶ/ር ገቢሳና ባልደረቦቻቸው እያካሄዱ ያሉት ምርምር መጠናከር ማሽላን የሚያጠቃውን ጥገኛ አረም አስመልክቶ ያለውን ዕውቀት የሚያሰፋ እንደሚሆን ተገልጿል።

ዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ ባካሂዱት ምርምርና የማዳቀል ሥራ ድርቅን መቋቋም የሚችል የማሽላ ዘር በማግኘታቸው ከሰሃራ በስተደቡብ ባሉ ሃገሮች ውስጥ የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካዊያን የምግብ እጥረትን ማሸነፍ እንዲችሉ ያደረጉ ሲሆን ለዚያ ውጤታቸው የዛሬ ስምንት ዓመት የዓለም የምግብ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

የዓለም የምግብ ሽልማት የምግብን አቅርቦትና ጥራት ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራትን ለሚያከናውኑ ሣይቲስቶችና ሌሎችም ባለሙያዎች የሚሰጥ ከፍ ያለ ክብር ያለው ሽልማት ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ ምርምር አምስት ሚሊየን ዶላር ተሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG