በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የፃፉት ደብዳቤ


ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ
ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ

በእስር ላይ የሚገኙት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የስዊድን ዜግነት ያላቸው የልብ ሃኪሙና የ“አዲስ የልብ ሕክምና ማዕከል” ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ “አሁንስ ፍትህ አገኝ ይሆን?” ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ደብዳቤ ፃፉ።

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የፃፉት ደብዳቤ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:20 0:00

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ በተመሠረተባቸው ክሥ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ለፍርድ ቤት በሰጡት የዕምነት ክህደት ቃል ተናግረው ሲከራከሩ ቆይተዋል።

በፍርድ ቤት የነበረው ክርክር አጠቃላይ ይዘት፤ ገቡ የተባሉትን ዕቃዎች በተመለከተ አስተዳዳራዊ ውሳኔ ተሰጥቶበት ከመታሰራቸ ከሁለት ዓመት በፊት የተዘጋ መሆኑን ይገልፃሉ። ዶ/ር ፍቅሩ ወደ ኢትዮጵያ ሊያስገቧቸው ሞክረዋል የተባሉት ቁሣቁስ አሮጌና እራሳቸው ከስዊድን ሆስፒታሎች በእርዳታ ያሰቧሰቧቸው ዋጋቸው ርካሽ የሆነ ክፍት የልብ ቀዶ ሕክምና በሚሠራበት ጊዜ ድጋፍ ሰጭ የሆኑ ብልቃጦች /ትዩቦች/ መሆናቸውን አስረድተው ተሟግተዋል።

አቶ አስቻለው አለማየሁ የተባሉ የቤተሰብ አባል ዶ/ር ፍቅሩ የዚህ ክስና ክርክር ጉዳይ ያበቃለት ነበር ይላሉ።

ዶ/ር ፍቅሩ የታሰሩት ለአምስት ዓመታት በመሆኑ በነፃ መሰናበታቸው በይግባኝ መቀየሩ እንኳን በእስር አያቆያቸውም ነበር ይሄኔ ከእስር መለቀቅ ነበረባቸው ይላሉ። ነገር ግን ዶክተር ፍቅሩ እዛው እስር ቤት እያሉ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አቃጥለዋል በሚል ከሌሎች 38 ተከሳሾች ጋራ ክስ ቀርቦባቸዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG