በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድሬደዋው ግጭት አራት ሰው ቆስሏል ተብሏል


በድሬዳዋ ከተማ በጥምቀት አከባበር በዓል ላይ ያልታወቁ ሰዎች በምዕመናን ላይ የፈፀሙትን ትንኮሳ ተከትሎ የተነሳው አለመረጋጋት ዛሬ ተባብሶ ቀጥሏል። ተቃውሞውም ሃይማኖትን ከመከላከል ወደ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተሻግሯል። በከተማው የታሰሩ ወጣቶች እንዲፈቱም ተጠይቋል። በዛሬው ዕለት በአብዛኞቹ የከተማዋ መንገዶች፣ የንግድ ማዕከላት የሆኑት ቀፊራ፣ ኮኔል፣ ታይዋን፣ ሩዝ ተራ፣ አሸዋና አካበቢው ያሉ መደብሮችና ባንኮችም ተዘግተው ውለዋል።

ዛሬ ጠዋት የአዲስ ከተማ ወጣቶችን የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ያነጋግራሉ ተብሎ በተስፋዬ ሜዳ ተሰብስበው የነበረ ቢሆንም፤ "ከንቲባው ግን 300 ተወካዮች ተመርጠው በአዳራሽ ውይይት እናካሂድ" ብለዋል መባሉ ከአዲስ አበባና ከሐረር ወደ ድሬዳዋ መግቢያ ብቸኛው የ"ሃይስኩል -ሼል" መንገድ እንዲዘጋ መንስዔ ሆኗል። ሆኖም በከንቲባው በኩል በአዳራሽ እንወያይ የሚል አማራጭ ብቻ ነበር ከመጀመሪያውም የቀረበው ተብሏል። አመፁ ቀስ በቀስ አድማሱን አስፋፍቶ እኩለቀን ለይ አብዛኛው የከተማዋን ሰፈሮች ያካለለ ሆኖ ውሏል፤ አመሻሽ ላይ ግን ብዙ አካባቢዎች የተረጋጉ ነበሩ።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በድሬደዋው ግጭት አራት ሰው ቆስሏል ተብሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:10 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG