ድሬዳዋ —
ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የጥምቀት በዓል ላይ የእግዚአብሔር አብ ቤተክርስትያን ታቦት ሲገባ በምዕመናን ላይ የተፈፀመውን ትንኮሳ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ከታሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎች መካከል 86ቱ ትናትናና ዛሬ አመሻሽ ላይ ክሰቸው ተቋርጦ ተለቀዋል፡፡
የፌደራል ዐቃቤ ህግ ወደ ፊትም ፋይላቸው እየተጣራ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች ሊለቀቁ ይችላሉ ብሏል፡፡ከተፈቱት መካከል የአስተዳደሩ ቦክስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ኤፍሬም ነጋሽ የሚገኝበት ሲሆን በልዩ ልዩ ኃላፊነት ላይ የነበሩ አምስት የአዴፓ አመራሮች መካከልም ሁለቱም ተለቀዋል ተብሏል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ