በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍርድ ቤት በዋስ እንዲፈቱ የወሰነላቸውን የ80 ዓመት አዛውንት ፖሊስ አስሮ አስቀምጧቸዋል ሲሉ ጠበቃውና ልጃቸው አማረሩ


አቶ ደቀቦ ዋረዮ
አቶ ደቀቦ ዋረዮ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዋስ እንዲፈቱ የወሰነላቸው አቶ ደቀቦ ዋሪዮ የተባሉ የ80 ዓመት አዛውንትን ፖሊስ አስሮ አስቀምጧቸዋል ሲሉ ጠበቃውና ልጃቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በሻሸመኔ ከተማ ነዋሪ የነበሩ አቶ ደቀቦ ዋሪዮ የተባሉ የ80 ዓመት አዛውንት ከእስር በዋስትና እንዲፈቱ ከአርባ ቀን በፊት ውሳኔ ቢሰጥም ፤ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ግን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቀብሎ ሊፈታቸው ባለመቻሉ አቶ ደቀቦ እስካሁን በእስር ላይ ናቸው ሲሉ ጠበቃቸውና ልጃቸው ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።

ጠበቃው "አካልን ነፃ የማድረግ ክስ" ሊያቀርቡ እንደሆነ ተናግርዋል።

ጽዮን ግርማ ስዊዘርላንድ የሚገኘውን ልጃቸውን አቶ በዳዳ ደቆየ እና ጠበቃውን አቶ ወንዱሙ ኢብሳንና አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG