በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከደወሌ ድሬዳዋ ተዘግቶ የነበረው መሥመር ተከፈተ


በአፋር ክልል ልዩ ኃይሎች የሚደርሰውን ጥቃት ለመቃወምና ሦስቱ አወዛጋቢ ቀበሌዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ ለመጠየቅ የኢሳ ሶማሌዎች በትላንትናው ዕለት ከድሬዳዋ ደወሌ የሚወስደውን መስመር ዘግተውት ነበር፡፡

በአፋር ክልል ልዩ ኃይሎች የሚደርሰውን ጥቃት ለመቃወምና ሦስቱ አወዛጋቢ ቀበሌዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ ለመጠየቅ የኢሳ ሶማሌዎች በትላንትናው ዕለት ከድሬዳዋ ደወሌ የሚወስደውን መስመር ዘግተውት ነበር፡፡ ሆኖም በትናንትናው ዕለት እስከሌሊቱ 7 ሰዓት ድረስ በቆዬ ድርድር መንገዱ እንዲከፈት ከሥምምነት ተደርሶ፣ በዛሬው ዕለት መንገዱ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል፡፡

እንደአቶ አደም ገለፃ ሰሞኑን በአፋር ልዩ ፖሊስ በተፈፀመው ጥቃት 18 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የአፋር ልዩ ኃይል ከሦስቱ ሶማሌ የሚበዛባቸው ቀበሌዎች እንዲወጣ ተወስኖ የነበረውም አዲሱ የአፋር ክልል አስተዳደርም ተስማምቶበት ነበር ይላሉ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከደወሌ ድሬዳዋ ተዘግቶ የነበረው መሥመር ተከፈተ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:45 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG