በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት የደርግ ባለሥልጣናት ከ30 ዓመታት በኋላ ነፃ ወጡ


የፌደራል ምክትል ዐቃቤ ሕግ ፈቃዱ ፀጋ
የፌደራል ምክትል ዐቃቤ ሕግ ፈቃዱ ፀጋ

በእነ ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም መዝገብ የተፈረደባቸው ሁለት ከፍተኛ የደርግ ባለሥልጣናት በአመክሮ እንዲለቀቁ የተወሰነው የሃገሪቱን ሕጎችና በዳኛች የተሰጠውን ትርጓሜ መሠረት በማድረግ መሆኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋ።

የውሳኔው መነሻ ደግሞ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ከነበረው ከነዚሁ ባለሥልጣናት የቀረበው አቤቱታ መሆኑን የፌደራል ምክትል ዐቃቤ ሕግ ፈቃዱ ፀጋ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማሪያም ግን እስካሁን ያቀረቡት አቤቱታ እንደሌለ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ጠቁመዋል።

በአመክሮ እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናት ለ30 ዓመታት በአዲስ አበባው የጣሊያን ኤምባሲ የቆዩት ሻለቃ ብርሃኑ ባይህ እና ሻለቃ አዲስ ተድላ ናቸው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሁለት የደርግ ባለሥልጣናት ከ30 ዓመታት በኋላ ነፃ ወጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:33 0:00


XS
SM
MD
LG