በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዴንማርኩ የሽብር ጥቃት ምርመራ ጀርመን ላይ ከተፈጸመ ሌላ እስር ጋራ ተገጣጠመ


የዴንማርክ ፖሊስ በፍሬድሪክስበርግ ከሚገኘው ፍ/ቤት ፊት ለፊት ቆሞ ይታያል፣ ኮፐንሃገን፣ ዴንማርክ እአአ ታኅሣሥ 14/2023
የዴንማርክ ፖሊስ በፍሬድሪክስበርግ ከሚገኘው ፍ/ቤት ፊት ለፊት ቆሞ ይታያል፣ ኮፐንሃገን፣ ዴንማርክ እአአ ታኅሣሥ 14/2023

በዴንማርክ፣ በሽብር ጥቃት የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለና ተጨማሪ አራት ግለሰቦችን እየፈለገ እንደኾነ፣ የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

የዴንማርኩ ክስ፣ ኔዘርላንድስ ላይ ከተፈጸመ የአንድ ተጠርጣሪ እስራት እና በጀርመን ውስጥ ከታሰሩ በርካታ የሐማስ ተጠርጣሪ አባላት እስር ጋራ ተገጣጥሟል። ይኹንና የዴንማርኩ እስር፣ ከሐማስ ጋራ ቁርኝት ይኖረው እንደኾን፣ ኮፐንሃገን እስከ አኹን ያለችው የለም።

ጀርመን በበኩሏ፣ ሦስቱ ታሳሪዎች፣ “በአውሮፓ በሚገኙ የአይሁዳውያን ተቋማት ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲዘጋጁ ተጠርጥረው የተያዙ ናቸው፤” ብላለች።

በተያያዘ በኔዘርላንድ፣ አንድ ሰው በቁጥጥር ሥር እንደዋለ፣ የዴንማርክ ባለሥልጣናት ቢናገሩም፤ በጀርመን በተያዙ የሽብር ጥቃት ተጠርጣሪ የሐማስ አባላት ላይ ከሚደረገው ምርመራ ጋራ ግንኙነት ይኑረው አይኑረው፣ እስከ አኹን የተገለጸ ነገር የለም፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG