አላማጣ —
የራያ “የማንነት ጥያቄ አለን” ብለው በትግራይ ደቡባዊ ዞን ኣላማጣ ከተማ ትናንት ሰልፍ በወጡ ወጣቶችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል።
ሕይወት የጠፋው ሰዎቹ በጥይት ተመትተው መሆኑን ከአላማጣ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
ቪኦኤ ያነጋገራቸው የክልሉ ምክር ቤት የአካባቢው እንደራሴዎች “የአላማጣ ህዝብ ያለው ጥያቄ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንጂ የማንነት አይደለም” ብለዋል።
በግጭቱ ውስጥ የተሣተፉ አካላት ሕግ ፊት እንደሚቀርቡ የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ተነስቷል የሚባለውን ጥያቄ ምንነትና ተገደሉ የተባሉ ሰዎችን ቁጥር በሚመለከት ከተለያዩ ምንጮች የተለያዩ መረጃዎች እየደረሱን በመሆኑ እማኞችን፣ የመንግሥትና የጤና ተቋማትንም ተጠሪዎች አካትተን ሰፋ ካለ ዘገባ ጋር እንመለሳለን።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ