ዋሺንግተን ዲሲ —
ትናንት ረቡዕ ለሦስተኛ ቀን በተካሄደው የዲሞክራቶች ጠቅላላ ጉባኤ ምሽት የካሊፎርኒያዋ ሰኔተር ከሚላ ኸሪስ የዕጩ ፕሬዘዳናት ጆ ባይደን አጋር ሆነው የተሰየሙበትን የምክትል ፕሬዚዳንትነት ዕጩነት ተቀብለዋል፡፡ በምሽቱ ተናጋሪዎች ከተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም በየሰው እጅ ባለው ጠመንጃና ሽጉጥ የሚደርሰው ጥቃት የአየር ጠባይ ለውጥ እና ኮቪድ-19 ዋነኞቹ ነበሩ፡፡
የቪኦኤ ዘጋቢ ማይክ ኦስሊቪያን “ሙሉ ሉሙሉ በድረ-ገጽ የተላለፈውን ዝግጅት የተከታተሉ ተመልካቾች ፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ እየተደጋገመ የቀረበውን ትችት ሲያደምጡ አምሽተዋል፡፡” በማለት የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሯል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።