በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራሲ በተግባር

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪክስ ቴሌርሰን ሰሞኑን እርሳቸውና አንድ ሌላ ረዳት ለጋዜጠኞች የሰጧቸውን አስተያየት ተከትሎ በቅርቡ ከትራምፕ አስተዳደር ሊሰናበቱ እንደሚችሉ እዚህ በዋሺንግተን አካባቢ በስፋት እየተገረ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪክስ ቴሌርሰን ሰሞኑን እርሳቸውና አንድ ሌላ ረዳት ለጋዜጠኞች የሰጧቸውን አስተያየት ተከትሎ በቅርቡ ከትራምፕ አስተዳደር ሊሰናበቱ እንደሚችሉ እዚህ በዋሺንግተን አካባቢ በስፋት እየተገረ ነው፡፡

ቴሌርሰን ባለፈው ሰኞ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ከምክትላቸው ከሚክ ፔንስ ጋር ለምሳ የተገናኙ ሲሆን ወደ ኋላ ደግሞ ሚክ ፔንስ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኒክ ሄሊ ጋር ተገናኝተዋል። የእነኝህ ሁለት ግንኙነቶች መገጣጠም ናቸው ስለ ዋይት ሃውስ የሚከታተሉ ወገኖችን ቀልብ የሳበውና ምናልባት ቴሌርሰን ሥልጣን ቢለቁ አምባሳደር ኒክ ሄሊ ሊተኳቸው እንደሚችሉ የተነጋገሩበት ነው ወደሚለው ግምት ያስገባችው።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪክስ ቴሌርሰን ከትራምፕ አስተዳደር እራሳቸውን ቢያገሉም ሆነ በፕሬዘዳንቱ ቢባረሩ በግማሽ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከዋይት ሃውስ የተሰናበቱትን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቁጥር ሥድስት ያደርሰዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዲሞክራሲ በተግባር
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:21 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG