በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት አብሮ በመኖር ዕጣ ላይ የተደቀነ ፈተና እና የሰላም ተስፋ


አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ እና ዶ/ር አወል ቃሲስ አሎ
አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ እና ዶ/ር አወል ቃሲስ አሎ

“አሁን ያለንበት ሁኔታ በተለይም ከጦርነቱ በኋላ ወደ ዲሞክራሲ ወደ ፖለቲካዊ ሽግግር ልንሄድ የምንችልበት ዕድላችን በጣም የተመናመነ ነው የሚመስለኝ።” ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ። “አሁን ትግራይ ውስጥ እየተደረገ ያለው ከቀበሌ ጀምሮ ህዝቡ የራሱን ሰዎች መርጦ ራሱን ማስተዳደር የሚችልበት መንገድ በኢትዮጵያ በሙሉ ሊደረግ የሚችለበት ሁኔታ ካልተፈጠረ ችግር ይኖራል። ያን ማድረግ አይቻልም ነበረ። አሁን ግን ወደ ዲሞክራሲ የመሄድ ዕድል አለ።” አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ።

በኢትዮያ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፡ በአንድ አገር ህዝብ አብሮ የመኖር ዕጣ ላይ የተደቀነ ፈተና፡ መንስኤዎቹ እና ወደፊት የሚያራምዱ መንገዶች፤ ክርክሩ ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጭብጦች ውስጥ ናቸው።

የክርክሩ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች በመጻፍ እና እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ትንታኔ በማቅረብ የሚታወቁት በሰሜን ምስራቅ ኢንግላንድ ከኒውካስል ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኘው የኪሊ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የህግ መምህርና ጸሃፊው ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ እና በሰሜን ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴሷ የማሳቹሴትስ ክፍለ ግዛት ጠበቃ መቅጠር ለማይችሉ ተከሳሾች የሕግ ጠበቃ የሚያቆመው ፐብሊክ ዲፌንደር የተባለው ድርጅት ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ ናቸው።

በቦስተን ከተማ በጥብቅና ሞያ የሚተዳደሩት አቶ ደረጀ ካሁን ቀደም በግዛቲቱ የተከላካይ ጠበቆች ማሕበር ፕሬዝዳንት እና ለዜጎች የነጻነት መብት የቆመው ማሕበር ሲቪል ሊበሪቲ ዩኒየን የማሳቹሴትስ ግዛት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆንም አገልግለዋል።

የክርክሩን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።

ክፍል አንድ፡- ግጭት አብሮ በመኖር ዕጣ ላይ የተደቀነ ፈተና የሰላም ተስፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:44 0:00
ክፍል ሁለት፡- ግጭት አብሮ በመኖር ዕጣ ላይ የተደቀነ ፈተና የሰላም ተስፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:28 0:00
ክፍል ሶሥት፡- ግጭት አብሮ በመኖር ዕጣ ላይ የተደቀነ ፈተና የሰላም ተስፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:30 0:00
ክፍል አራት፦ ህገ መንግሥት፣ ፌደራሊዝም፣ የግለሰብ እና የቡድን መብት
please wait

No media source currently available

0:00 0:23:57 0:00



XS
SM
MD
LG