በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታጣቂዎች የታገቱት የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አለመለቀቃቸው ተገለጸ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ
በታጣቂዎች የታገቱት የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አለመለቀቃቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:21 0:00

ባለፈው ሳምንት ሰኞ፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ በታጣቂዎች መታገታቸው የተነገረው ከአንድ መቶ በላይ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ እስከ አሁን አለመለቀቃቸው ከእገታ እንዳመለጡ የተናገሩ ተማሪዎች ።

ከእገታ እንዳመለጡ የተናገሩ ተማሪዎች፣ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ሁለት አውቶብሶችን ሞልተው በተነሡ በሦስተኛው ቀን ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረ ጉራቻ አካባቢ ሲደርሱ፣ "የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ናቸው" ያሏቸው ታጣቂዎች፣ ከእነርሱ ጋራ በሦስት አውቶቡሶች ተሳፍረው የነበሩ ተጓዦችን አግተው እየደበደቡ ወደ ጫካ እንደወሰዷቸው ለአሜሪካ ድምፅ

ከታገተ ከአንድ ቀን በኋላ የገለጸልን፣ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት ተማሪ፣ ከአጋቾቹ መካከል አንዱ መጥቶ “ስለ ሸኔ ታውቃላችኹ?” በማለት በአፋን ኦሮሞ እንደጠየቃቸውና በአፋን ኦሮሞ የመለሱለትን ተማሪዎች እንዲለቀቁ ማድረጉን ተናግሯል።

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰሎሞን አበበ የእጅ ስልክ ላይ ደውለን፥ "ተማሪዎች ተለቀዋል" የሚል አጭር መልስ ከሰጡን በኋላ ስልኩን ዘግተውታል።

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስማማው ዘገየን በስልክ አግኝተናቸው፥ "ጉዳዩን እየተከታተልን ነው፤ ልጆቹ ግን የታገቱት በኦሮሚያ ክልል ስለኾነ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቁ፤" ብለዋል። ከትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ግን አልተሳካም።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ፣ ለገንዘብ ጥቅም ሲባል ተማሪዎችንና ሰላማውያን ዜጎችን የማገት ድርጊት እንዲቆምና የሕግ የበላይነት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG