በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ በተፈፀመ የአየር ድብደባ 44 ሰዎች ተገደሉ


ትናንት ሰኔ 25/2011 ዓ.ም ምሽት ከሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ወጣ ብሎ በሚገኝ ታጃውራ በተባለ ፍልሰተኞች በታሰሩበትና ጥቃቱ የተፈፀመብት ቦታ/ ፎቶ፡ ኤፒ
ትናንት ሰኔ 25/2011 ዓ.ም ምሽት ከሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ወጣ ብሎ በሚገኝ ታጃውራ በተባለ ፍልሰተኞች በታሰሩበትና ጥቃቱ የተፈፀመብት ቦታ/ ፎቶ፡ ኤፒ

ከሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ወጣ ብሎ በሚገኝ ታጃውራ በተባለ ፍልሰተኞች በታሰሩበት ቦታ በተፈፀመ የአየር ጥቃት እስካሁን 44 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። 130 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የተባበሩትን መንግሥታት ድርጅት ድርጊቱን በእጅጉ አውግዞታል። ጥቃቱ በደረሰበት እስር ቤት የሚገኙ ኤርትራውያን ስለ አደጋው ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ ፤ በአየር ድብደባው ሕይወታቸውን ካጡት ውስጥ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን "የሉበትም" ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ይህንን ጥቃት በእጅጉ አውግዘዋል። አያይዘውም በመጀመሪያ ስደተኞችና ፍልሰተኞች ሊታሰሩ አይገባም፣ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላም ሰላማዊ ዜጎችና ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ መሆን የለበትም ብለዋል። አክለውም በሜዲትራንያን ባህር በኩል አውሮፓ ለመግባት ሞክረው ከአደጋ እንዲተርፉ የተደረጉትን ፍልሰተኞች ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ ሊገደዱ አይገባም። "ምክንያቱም ሊቢያ ለደህንነታቸው አስተማማኝ ሀገር አይደልችምና” ፊሊፖ ግራንዲ አሳስበዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በሊቢያ በተፈፀመ የአየር ድብደባ 44 ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:56 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG