ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት እየደረሰ ያለው ዕለታዊ የሞት ጉዳት ሰኔ 24 አካባቢ ከአሁኑ በእጥፍ ሊያሻቅብ እንደሚችል የመንግሥቱ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ተቋም ያወጣውን የጥናታዊ ትንበያ ሰነድ ዋይት ሃውስ አጣጥሎታል።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እስካሁን ለአዲሱ ክኮሮናቫይረስ እየታገለጠ ያለው 25 ሺህ የሚደርስ ቁጥር ያለው ሰው እንደሆነ ይነገራል። የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት /ሲዲሲ እንደሚለው ደግሞ የያዝነው የአውሮፓ ወር ሜይ መጨረሻ አካባቢ ዕለታዊ የመጋለጥ መጠን ወደ 2መቶ ሺህ እንደሚያሻቅብ ተንብያል።
ይህንን የራሱን የመንግሥቱን ትንበያ ግን የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ ጄዱ ዲሪ እንደማይቀበሉት ተግረዋል። የዋይት ኃውስ መግለጫ ቁጥሩ እንደሚጨምር ባያስተባብልም ሊሆን የሚችለው አሁን ካለበት 1ሺህ 7መቶ በወሩ መጨራሻ ሦስት ሺህ ቢደርስ እንደሆነ ያመለክታል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።