በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእነአቶ ዮሐንስ ቧያለው ክስ በችሎት ተነበበ


የእነአቶ ዮሐንስ ቧያለው ክስ በችሎት ተነበበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:25 0:00

የእነአቶ ዮሐንስ ቧያለው ክስ በችሎት ተነበበ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሕገ መንግሥት እና ሽብር ወንጀል ችሎት፣ በዛሬ ሰኞ ውሎው፣ በእነአቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ የሽብር ተከሳሾችን ክስ በንባብ መስማቱን ጠበቃው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ተከሳሾቹ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ተፈጸመብን ባሉት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ፣ ኢሰመኮ ምርመራ አድርጎ ለቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠቱንም፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም፣ በአማራ ተወላጅ ታሳሪዎች ላይ በማረሚያ ቤት እየተፈጸመ ነው ያሉትን መድልዎ በመቃወም የረኀብ አድማ አድርገዋል ያሏቸው አቶ ክርስቲያን ታደለ ባቀረቡት አቤቱታም ላይ ትዕዛዝ መሰጠቱን ጠበቃው ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG