በሌላ በኩል፣ ተከሳሾቹ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ተፈጸመብን ባሉት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ፣ ኢሰመኮ ምርመራ አድርጎ ለቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠቱንም፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም፣ በአማራ ተወላጅ ታሳሪዎች ላይ በማረሚያ ቤት እየተፈጸመ ነው ያሉትን መድልዎ በመቃወም የረኀብ አድማ አድርገዋል ያሏቸው አቶ ክርስቲያን ታደለ ባቀረቡት አቤቱታም ላይ ትዕዛዝ መሰጠቱን ጠበቃው ገልጸዋል፡፡