በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእነአቶ ጀዋር መሀመድ ጉዳይ ለማክሰኞ ተቀጠረ


ፎቶ ፋይል፦ አቶ ጀዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባ
ፎቶ ፋይል፦ አቶ ጀዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባ

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነአቶ ጀዋር መሀመድ የግል ህክምና ላይ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ይግባኝ ያየው ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 16/2013 ዓ.ም ቀጥሯል።

በሌላ በኩል በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የህክምና ቦታ ጉዳይ ቀደም ሲል የሰጠውን ትዕዛዝ ለምን እንዳላስፈፀመ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ቀርቦ እንዲያብራራ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማረሚያ ቤቱ አዛዥ ባለመቅረባቸው አዛዡ በአካል እንዲቀርቡ በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጥቶ ለየካቲት 16/2013 ዓ.ም. ቀጥሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የእነአቶ ጀዋር መሀመድ ጉዳይ ለማክሰኞ ተቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00


XS
SM
MD
LG