የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ፣ ዛሬ በቀጠሮ ፍርድ ቤት የቀረቡ ጋዜጠኞች እና ሌሎች የሚዲያ ሠራተኞች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ለውሳኔ ተቀጠረ።
ፍርድ ቤቱ እስረኞቹ በዋስትና ይለቀቁ አሊያም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ይፈቀድለት በሚለው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቆቻቸው ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡
የሚዲያ ባለሙያዎች እስራት ከተለያዩ አካላት ቅሬታ ቢያስነሳም፣ መንግስት እርምጃው ሕግ የማስከበር ተልዕኮ አካል እንደሆነ መግለጹ አይዘነጋም፡፡
ዘገባው የኬኔዲ አባተ ነው።