በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ምግብ ድርጅት 150 ምግብ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ደርሰዋል አለ


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ድርጅት እርዳታ የጫኑ ከ150 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን አስታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትናንት በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ ከ5.2 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ የሚፈልገውን መጠነ ሰፊ እርዳታ በየእለቱ እየላከ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው ባለ ግጭት ወደ አንድ ወር ለተጠጋ ጊዜ ወደ ትግራይ የሚያስገባው መንገድ ተዘግቶ የቆየ መሆኑን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ ወደ በአማራ ክልልም በደሴና ኮምቦልቻ ለሚገኙ 100ሺ ተፈናቆዮች ባላፈው ሳምንት የምግብ እርዳታ መከፋፈሉን ተናግረዋል፡፡

በእነዚህ ከተሞችም እርዳታ ሲሰጥ በአንድ ወር በተቃረበ ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ነው ብለዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ የዓለም ምግብ ድርጅትና አጋሮቹ ወደ 450ሺ ለሚደርሱ ሰዎች የምግብ እርዳታ የሚያቀርቡ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው ባለ አለመረጋጋት የተነሳ በኢትዮጵያ ሰአብአዊ ምላሽ ለመስጠትአሁንም ችግር እንደሆነ መቀለጡን ዋና ጸሀፊው አመልክተዋል፡፡

የዓለም ምግብ ድርጅት በ1ሺ700 ተሽካርካሪዎችን ሊጫን የሚችል ከ67ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆን እህል በሰሜን ኢትዮጵያ ያከማቸ መሆኑም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

ይህወደ 3.7ሚሊዮን የሚሆን ህዝብን ለሁለት ወር መመገብየሚችል መሆኑን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የገንዘብና የነዳጅ እጥረት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG