ዋሽንግተን ዲሲ —
የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋም ሥራ ላይ የተሰማሩ አንድ የሀገር ሽማግሌ በበኩላቸው “እንዲህ ያለ ግጭት ከዚህ ቀደም አንድም ጊዜ አጋጥሞን አያውቅም በአስቸኳይ ወደ ቀደመው ሰላማዊ ግንኙነታችን ልንመለስ ይገባል” ብለዋል።
የአካባቢው አስተዳደር በግጭቱ የተፈናቀሉ ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው፤ “በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ላሉት ለዕለት የሚያስፈልጋቸው ነገር እየተሟላ ነው” ብለዋል።
የኦፌኮና የአረና ትግራይ ፓርቲ አመራሮች ይህ ችግር የኢሕዴግ ውጤት ነው ካሉ በኋላ “የኢትዮጵያ ሕዝብ
"ከኢሕአዴግ በፊትም በጋራ ይኖር ነበር ፣ በኢሕአዴግ ጊዜም በጋራ እየኖረ ነውና ይህ የአብሮነት ግንኙነቱ እንዳይጎዳ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት” ብለዋል።
ሁሉንም ያነጋገርችው ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ