በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮልን ፓወል ከፍተኛው ጀኔራል ከፍተኛው ዲፕሎማት!


ኮልን ፓወል የመጀመሪያው ጥቁር የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከፍተኛው የጦር መሪ ነበሩ
ኮልን ፓወል የመጀመሪያው ጥቁር የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከፍተኛው የጦር መሪ ነበሩ

ኮልን ፓወል የመጀመሪያው ጥቁር የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከፍተኛው የጦር መሪ ነበሩ፡፡ ትናንት ሰኞ፣ በ84 ዓመታቸው፣ በኮቪድ 19 ሳቢያ በተወሳሰበ የጤንነት ችግር፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አሳዛኙን የኮልን ፓወል ሞት በፌስ ቡክ ያረዱት ቤተሰቦቻቸው “እጅግ ተወዳጅ የሆነውን ባል፣ አባት፣ አያትና ትልቅ አሜሪካዊ አጥተናል፡፡” ብለዋል፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ የዩናዩትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና አሜሪካውያን ሀዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡

ጀኔራል ፓወል እኤአ ከ2001 እስከ 2005 ድረስ በሪፐብሊካኑ ጆርጅ ደብሊዩ ቡሽ የመጀመሪያው የሥልጣን ዘመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

ኮልን ፓወል ከፍተኛው ጀኔራል ከፍተኛው ዲፕሎማት!
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:30 0:00

ከዚያ ቀደም ሲል ከፍተኛው ወታደራዊ ጀኔራል ነበሩና፣ ወደ ሲቪሉ ውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ተዛውረው ሲመጡ፣ የገጠማቸውን ነገር፣ ኮልን ፓወል እንደሚከተለው ገልጸውት ነበር፡፡

“ቢሮዬ ውስጥ ተቀምጨ ነበር፡፡ አንድ ከፍተኛ የሠራዊቱ አባል ወደ ቢሮዬ መጥቶ በሩን ዘጋውና እንዲህ አለኝ”

እባክዎ አንድ ነገር ልጠይቅዎ ነበር፣ እዚህ ህንጻ ውስጥ ብዙ ውዥንብሮች አሉ፡፡”

“ምንድነው እምትለው፣ ምን ተፈጠረ?” አልኩት፡፡

ጌታዬ እንዴት ብለን ነው የምንጠራዎት? ሚስተር ሴክሬተሪ ብለን ነው ወይስ ጀኔራል ብለን ነው?

“በየትኛው መንገድ ቢሆን ሚስተር ሴክሬተሪ ነው እምባለው፡፡” አልኩትና “በል አሁን አስር ፑሽ አፕ ሥራ!”

የቀድሞ ፕሬዚዳንትና ባለቤታቸው ሎራ ቡሽ በኮልን ፓወል ሞት በእግጁ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

“በቬትናም ጦርነት ውትድርናን ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ትልቅ የህዝብ አገልጋይ ነበሩ፡፡” ያሉት ቡሽ “ብዙ ፕሬዚዳንቶች በኮልን ፓወል ምክርና ልምድ የሚተማመኑ ነበሩ፡፡ በፕሬዚዳንቶች የተወደዱ ሰው በመሆናቸውም ሁለት ጊዜ የፕሬዚዳንታዊውን የነጻነት ሜዳልያ ተሸልመዋል፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም እጅግ የተከበሩ ነበሩ፡፡” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ ተወዳዳሪ የሌለው ክብርና ሞገስ ያላቸው አርበኛ ነበሩ” በማለት ገልጸዋቸዋል፡፡

አይያዘውም ባይደን እንዲህ አሉ

“ኮልን የሁለቱም ከፍተኛው ተዋጊና ዲፕሎማት ተምሳሌት ናቸው፡፡ ከምንም በላይ ለአገራችን ደህንነትና ጥንካሬ ቁርጠኛ ነበሩ፡፡ በውጊያ ውስጥ እንደማለፋቸው ወታደራዊ የበላይነትም ሰላምና ብልጽግናን ለማምጣት በቂ አለመሆኑን ከማንም በለያ የተገነዘቡ ሰው ነበሩ፡፡”

ኮልን ፓወል እኤአ በ2008 ከፓርቲያቸው ከሪፕብሊካን ፓርቲ በመለከት በወቅቱ ፕሬዚዳንታዊ እጩ የሆኑትን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ደግፈዋል፡፡

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማም እንዲሁ ሀዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኦባማ ትናንት ሰኞ ባወጡት መግለጫ

“ጀኔራል ኮልን ፓወል ለዚህ አገር የሚጠቅመው መልካም ነገር ምን እንደሆነ የተረዱ ሰው ነበሩ፡፡ ህይወታቸውን፣ አገልግሎቶቻቸውንና በየአደባባዩ የሚናገሩትን ነገር ሁሉ አንድ አድርገው ለማሳየት የሚጥሩ ነበሩ፡፡ ሚሸል እና እኔ ሁልጊዜም የምናያቸው አሜሪካና አሜሪካውያን ምን መምሰል፣ ምንስ መሆን እንደሚችሉና እንዳለባቸው ምሳሌ አድርገን የምንመለከታቸው ሰው ነበሩ፡፡ “ብለዋል፡፡

የዩናትድ ስቴትስ የመከካለያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን በትዊተር ባወጡት መልዕክታቸው “ጀኔራል ፓወልን መተካት አይቻልም፡፡” በማለት ፓወል የቅርብ ጓደኛቸውና አማካሪያቸው እንደነበሩ እንዲህ በማለት መስከረዋል

“ሁልጊዜ ለኔ ጊዜ ይኖረዋል፡፡ ብርቱ ጉዳዮች ሲገጥሙኝ ሁሌም ወደሱ እሄዳለሁ፡፡ ሁልጊዜም ትልቅ ትቅል መካሪ ነው፡፡ በርግጠኝነት እናጣዋለን፡፡ ልቤ እንደተሸነቆረ ሆኖ ይሰማኛል፡፡”

ኮልን ፓወል ባለ አራት ኮከብ ጀኔራል የ35 ዓመታት አርበኛና የፔንታገን ወታደራዊ መሪ፣ አዛዥ ነበሩ፡፡ እኤአ ከ1989 እስከ 1993 በመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ቡሽ (አባትየው) ዘመን ኤታማዦር ሹም የነበሩ ሲሆን እሳቸውን በተኳቸው ፕሬዚዳንት ክሊንተን ዘመንም ለወራት በዚያው ሥልጣንና ኃላፊነት አገልግለዋል፡፡

ፓወል ከነዚህም ሁሉ በፊት እኤአ ከ1987 እስከ 1989 በፕሬዚዳንት ሬገን ዘመን የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እንዲህ ይላሉ

“የሴክሬተሪ ፓወል የውትድርና ዓመታት ለዚያ ለተለየው የዲፕሎማሲ ብቃታቸው፣ አስተዋጽኦ ያደረጉ ይመስለኛል፡፡ ጦርነትና ወታደራዊ እርምጃ ሁል ጊዜም የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን ያውቁ ነበር፡፡”

ኮልን ፓወል እኤአ በ1991 ኩዌትን ከሳዳም ሁሴን ወረራ ፈጥነው በማዳን የጦር አመራራቸው በወቅቱ ተደንቀዋል፡፡ ተችዎች እንምደሚሉት ፓወልን ለትችት የዳረጋቸው የኢራቁ ጦርነት ነው፡፡

ፓወል እኤአ የካቲት 5 2003 የተባበሩት መንግሥታትን የጸጥታ ምክር ቤት ፊት ለፊት ቀርበው ዩናይትድ ስቴትስ ኢራቅን ስለመወረር ያላትን እቅድ በይፋ ተናግረዋል፡፡

ኢራቅ ባሳየቸው ባህርይ የተገለጸው ነገር ሳዳም ሁሴንና አስተዳደራቸው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መሰረት የአውዳሚ የጦር መሳሪያ ፕሮግራማቸውን ለመተው ምንም ጥረት አላደረጉም፡፡

እኤአ መስከረም በ2005 ስለኢራቅ አውዳሚ የጦር መሳሪያ የነበራቸው መረጃ የተሳሳተ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የጦር መሳሪያዎች ቁጥጥር ማዕክል ጆን አይዛክ ግን እንዲህ ይላሉ

ያ ምናልባት በህይወት ታሪካቸው ላይ የሚያጠላ ትልቁ ስህተት ይሆናል የሳቸው ስህተት ብቻ ግን አይደለም፡፡ የጠቅላላው የመረጃ ማህበረሰቡ ስህተት ነው፡፡ እንደሚመስለኝ 13 የተለያዩ የመረጃ ማዕከላት ናቸው፡፡ ከ13ቱ 12ቱ “ኢራቅ አውዳሚ የጦር መሣሪያዎች አሏት” ብለው ተናገሩ፡፡ ስለዚህ እነሱ ያሉትን ካጠኑ በኋላ ወደ መስማማቱ መጡ፡፡ ሁሉም ስህተት ነበሩ፡፡

ስህተታቸውን ለመግለጽ ምን ጊዜም ወደ ኋላ የማይሉት ኮልን ፓወል አንድ ወቅት በቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ “ይህ ሁሉጊዜም በህይወት ታሪኬ ተመዝግቦ ይቀጥላል፣ ይህ ደግሞ በጣም ያም ነበር ፣ አሁንም ያማል” ብለው ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG