በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ዲፕሎማት እና የጦር መሪ ኮልን ፓወል አረፉ


ፎቶ ፋይል፦ ጄኔራል ኮልን ፓወል የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቁር አሜሪካዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የቀድሞ የጦር ኃይሎች ኤታ ማዦር ሹም
ፎቶ ፋይል፦ ጄኔራል ኮልን ፓወል የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቁር አሜሪካዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የቀድሞ የጦር ኃይሎች ኤታ ማዦር ሹም

ጄኔራል ኮልን ፓወል የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቁር አሜሪካዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የቀድሞ የጦር ኃይሎች ኤታ ማዦር ሹም በዛሬው ዕለት አረፉ።

የሰማኒያ አራት ዓመቱ ኮልን ፓወል ህይወታቸው ያለፈው በኮቪድ-19 በተያያዘ ህመም ሳቢያ መሆኑ ተገልጿል።

ቤተሰባቸው በፌስቡክ ገጽ ላይ ስለህልፈታቸው ባወጣው መግለጫ

"ግሩም ሰው፥ ባለቤታቸውን የሚያፈቅሩ፥ አባት፥ አያት እና ታላቅ አሜሪካዊ አጥተናል" ብሏል።

ኮልን ፓወል የኮቪድ-19 ክትባታቸውን ሙሉ በሙሉ ተከትበው እንደነበር ያስታወቁት ቤተሰቦቻቸው፣ ከዋሽንግተን ወጣ ብሎ በሚገኘው የዎልተር ሪድ ብሄራዊ የህክምና ማዕከል ስለተሰጣቸው ህክምና እና እንክብካቤ ምስጋና አቅርበዋል።

ፓወል በሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ የመጀመሪያው ዘመነ መንግሥት እአአ ከ2001 እስከ 2005 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ።

ባለ አራት ኮከቡ የጦር ሠራዊት ጀኔራል ከዚያ አስቀድመው በፕሬዚዳንት ጆርጅ ሄርበርት ዋከር ቡሽ አስተዳደር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ሆነው አገልግለዋል።

XS
SM
MD
LG