በዩናይትድ ስቴትስ ሜን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የወጣ ሪፖርት እንደጠቆመው ወባ ወትሮ ሊተላለፍባቸው የማይችሉ የነበሩ በከፍተኛ ሥፍራዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለቢምቢ መራባትና ለወባ ሥርጭት እየተጋለጡ መሆናቸውን ተመራማሪዎቹ አመልክተዋል፡፡
ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በተካሄዱ ተከታታይ ጥናቶች መሠረት ለወባ ተጋላጭ የሚሆኑት አካባቢዎች ከወትሮዎቹ ቆላማ ሥፍራዎች እስከ መቶ ሜትር ከፍታ ድረስ የሚገኙ ሥፍራዎችንም ሊሸፍን እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ወባ አምጭ የሆኑ ሁለት ዋነኛ የሚባሉ ጥገኛ ሕዋሣት ለመራባትና ለመተላለፍ ከ15 እስከ 18 ዲግሪስ ሴልሽየስ የሚደርስ ተከታታይ የሙቀት መጠን እንደሚፈልጉና ወይና ደጋና ደጋማዎቹ አካባቢዎች ለዚህ ዓይነት የሙቀት መጠን እየተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶቹ አሳይተዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ በምሽቱ የጤና ዝግጅታችን ተካትቷል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ