በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድን ስምምነት ተከትሎ ቻይና የሶማሊያን 'አንድነት' እንደምትደግፍ አስታወቀች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በኢትዮጵያ እና በተገንጣይዋ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገው የባህር ወደብ ስምምነት ቀጠናዊ ውጥረት ማስነሳቱን ተከትሎ፣ ቻይና የሶማሊያ "የግዛት አንድነት" እንዲከበር ሐሙስ እለት ጥሪ አቅርባለች።

ታህሳስ 22 ቀን በተፈረመው የጋራ መግባቢያ ሰነድ፣ ሶማሊላንድ 20 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የባህር ጠረፏን፣ ወደብ አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ ለ50 ዓመት እንድትከራይ የተስማማች ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የባህር ኃይል የመመስረት እና የንግድ ወደብ የማቋቋም ፍላጎት እንዳላት ተመልክቷል።

የቀድሞ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት የነበረችው ሶማሊላንድ እ.አ.አ በ1991 ከሶማሊያ ነፃ መሆኗን ብታውጅም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እስካሁን እውቅና አልሰጣትም።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማኦ ኒንግን ጠቅሶ፣ በኤክስ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መልዕክት ያስተላለፈው በሶማሊያ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ፣ "ሶማሊላንድ የሶማሊያ አካል ነች" ብሏል።

"የሶማሊያ መንግስት ብሄራዊ እንድነቱን፣ ሉዓላዊነቱን እና ግዛቱን ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት፣ ቻይና የሶማሊያን የፌደራል መንግስት ትደግፋለች" ያለው መግለጫ አክሎ "የቀጠናው ሀገራት፣ ቀጠናዊ ጉዳዮችን፣ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንደሚያስተናግዱት ተስፋ አለን" ብሏል።

የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት(ኢጋድ) በበኩሉ ሐሙስ እለት ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ስላለው አለመግባባት እና ከሚያዚያ ወር ጀምሮ በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን ስላለው ሁኔታ ለመወያየት እ.አ.አ ጥር 18 ኡጋንዳ ላይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ከቻይና በተጨማሪ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአረብ ሊግ፣ ግብፅ እና ቱርክ የሶማሊያ ሉዓላዊነት እንዲከበር ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG