በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ጭካኔ በዜጎች ላይ በጅምላ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ብዙዎችን ለሕልፈትና ለከፋ አደጋ እየዳረጉ ነው። በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፤ በግለሰቦች እና በሕዝብ ንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ ተፈጽሟል።
አሁንም ድረስ ያላበቁት ጥቃቶች በአንጻሩም በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ሃዘን እና ቁጣ ቀስቅሰዋል። አንዳንዴም ዘውግ ለይተው ጭምር የሚቃጡት እነኚህ ዘግናኝ ጥቃቶች በአስቸኳይ ይቆሙ ዘንድ የእምነት ቤቶች ምን ዓይነት ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ? የጥቃቶቹ ምንነት በወጉ እንዲጣራና ወንጀለኞቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚሉት ጥያቄዎች ከየአቅጣጫው እየተሰሙ ነው።
ለጥያቄዎ መልስ ጥቃቶቹ እንዲቆሙና ለዚህን መሰሉ ድርጊቶች ዘለቄታ ያለው መፍትሔ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የእምነት ቤቶችን ሚና አስመልክቶ ከአድማጮች ለደረሱን ጥያቄዎች ምላሽ ከሁለት ሃይማኖት አባቶችና ከአንድ የማሕበረሰብ መሪ ጋር የተካሄደ ውይይት ነው።
ተከታታይ ውይይቱን ከዚህ ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ