በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጥያቄዎ መልስ


የሰብዓዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶችና ተቃዋሚ ኃይሎች፣ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የሄደውን የዜጎች እንግልት፣ እስራትና መገደል በመጥቀስ፣ የኢትዮጵያን መንግሥት ሲተቹ መቆየታቸው ይታወቃል። ካለፈው መስከረም ወዲህ ግን የዜጎች ሕይወት የሚጠፋው በመንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ሕዝብ ወርዶ የእርስ በርስ የመገዳደል መልክ መያዙ፣ የኢትዮጵያን ሁናቴ እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል።

የሰብዓዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶችና ተቃዋሚ ኃይሎች፣ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የሄደውን የዜጎች እንግልት፣ እስራትና መገደል በመጥቀስ፣ የኢትዮጵያን መንግሥት ሲተቹ መቆየታቸው ይታወቃል።

ካለፈው መስከረም ወዲህ ግን የዜጎች ሕይወት የሚጠፋው በመንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ሕዝብ ወርዶ የእርስ በርስ የመገዳደል መልክ መያዙ፣ የኢትዮጵያን ሁናቴ እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል። ይህን አገኛ አዝማሚያ ለመቀልበስ ከመንግሥት፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከማኅበረሰብ መሪዎችና ከአክቲቪስቶች ምን ይጠበቃል?

በሁከቱ ዙሪያ፣ ከእናንተ ከአድማጮቻችን የሰበሰብናቸውን ጽያቄዎች ሊመልሱልን ቃል ከገቡት ሁለት ምሑራን መካከል ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማርያምን አግኝተናል።

ዶክተር ያዕቆብ፣ ከጡረታ በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂንያ ጠቅላይ ግዛት /Norfolk State University/ የንግድ ሕግ ፕሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል።

በ1990«ዎቹ» የሩዋንዳ የዘር ጅምላ ፍጅት ደግሞ፣ በዓለማቀፉ የወንጀል ችሎት ዋና ዐቃቤ-ህግ ሆነው አገልግለዋል። በ1997«ኡ» የኢትዮጵያ ምርጫ፣ ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክረሲ ፓርቲ እጩዎች አንዱ በመሆን፣ በምርጫውም ባለ ድል እንደነበሩና፣ በኋላም ከሌሎች መሪዎች ጋር ለእስር መዳረጋቸው አይዘነጋም።

ሌላው ሊቀርቡልን ቃል ገብተውልን የነበሩት የኢፌዴሪ መንግሥት ኰሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽ/ቤት የሚዲያ ልማትና ብዝሃነት ዳይሬክተር ጅንናር አቶ ታምራት ደጀኔ ነበሩ። በሰጡን ቀጸሮ መሠረት ብንደውል ልናገኘው አልቻልንም። ይቅርታ እንጠይቃለን።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለጥያቄዎ መልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:33:15 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG