በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሊፎርኒያ ሳን በርናርዲኖ ተኩስ ከፍተው አስራ አራት ሰው የገደሉት አጥቂዎች ማንነት ታወቀ


ትናንት ረቡዕ ዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ ክፍለ ሀገር San Brnardino ከተማ በኣንድ የማህበራዊ እገልግሎት ማዕከል ተኩስ ከፍተው ኣስራ ኣራት ሰዎች በመግደል የተጠረጠሩትን ሁለት ሰዎች ማንነት የከተማዋ ባለስልጣናት ኣረጋግጠዋል። በጥቃቱ ሌሎች ኣስራ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል።

የሳን በርናርዲኖ ወረዳ የጤና ቢሮ ሰራተኞች ከሎስ ኣንጀለስ ከተማ በስተ ምስራቅ ዘጠና ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ኢንላንድ ሪጅናል ሰንተር (Inland Regional Center) በሚባለው ማዕከል የዓመት በዓል ግብዣ ላይ እየተደሰቱ ሳሉ ነው አውቶማቲክ መሣሪያ የያዙ አንድ ወንድና ኣንዲት ሴት ገብተው ተኩስ የከፈቱት ።

የሳን በርናርዲኖ ፖሊስ ኣዣዥ ዣሮድ ቡርጉዋን እንዳሉት አጥቂዎቹ ሳኢድ ፋሮክ የተባለ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተወለደ የሃያ ስምንት ወጣትና ታሽፊን ማሊክ የተባለች የሀያ ሰባት ኣመትዋ ባለቤቱ ወይም እጮኛው ነች።

“ሚስተር ፋሩክ የወረዳው ሰራተኛ ነው። በህዝብ ጤና ጥበቃ ክፍል የእካባቢ ደህንነት ስፔሺያሊስት ሲሆን ለኣምስት ዓመታት ሰርቱዋል።

ግብዣው ላይ ነበር ። ከዚያም በሆነ ምክንያት ንዴት ይታይበት እንደነበርና ድንገት ብድግ ብሎ ጥሎ እንደወጣ ነው የተገለጸው።” ብለዋል የሳን በርናርዲኖው ፖሊስ አዛዥ።

ኣጥቂዎቹን ፖሊሶች ተከታትለው በኣቅራቢያው በሚገኝ ከተማ ባለ መኖሪያ ቤት ደርሰውባቸው በመኪና ሲያይሳዱዋቸው በተካሂደ ተኩስ ልውልልውጥ ሁለቱም ፋሩክ እና ማሊክ ተገድለዋል።

ሁኔታውን በተመለከትነው እና በያዙት ትጥቅ ዓይነት ተመርኩዘን ለመናገር በተወሰነ ደረጃ ዝግጅት የተደረገበት ጥቃት ይመስለኛል። ስለዚህ እንዲሁ ድንገ ትሮጥ ብለው ወደቤት ሄደው እንደዚያ ዓይነት የታክቲክ ልብሶች ለብሰው መሳሪያ ብድግ ኣድርገው ኣድርገው ተመልሰው የሄዱበት ሁኔታ አልነበረም።” ሲሉ የፖሊስ ኣዛዡ አስረድተዋል።

የሳኢድ ፋሮክ የእህቱ ባል የሆነው ፋርሃን ካን የእሜሪካውያን የእስላማዊ ግንኙነቶች ምክር ቤት የሎስ አንጀለስ ቅርንጫፍ በጠራው ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ ቀርቦ ለጥቃቱ ሰለባዎች ቤተሰቦች ሃዘኑን ገልጹዋል።

“በደረሰው ነገር በጣም ደንግጫለሁ። ይህን ብቻ ነው የምለው። በዚህ ጥቃት የተጎዳችሁ ሁሉ …ሁላችሁም እንደምትረዱ ታስፋ ኣደርጋለሁ ፈጥናችሁ እንድትጽናኑም እመኛለሁ።” ብሉዋል።

የጥቃቱ ዜና በተነገረበት ወቅት ጥቃቱ በሲ ቢ ኤስ ቴሌቭዥን ቃለ መጠይቅ ላይ የነበሩት ፕረዚደንት ባራክ ኦባማ አሁንም እንደገና ሌላ የጅምላ ተኩስ ጥቃት በመድረሱ ማዘናቸውን ገልጸዋል።

“ይህን ያሁኑን ጥቃት በቁጥጥር ስር ማዋል እንችላለን ብዬ ተስፋ ኣደርጋለሁ። አጥቂዎቹ የተነሳሱበት ምክንያት ምን እንደሆነ ገና ኣላወቅንም። የአሜሪካውያንን ደህንነት በተሻለ ለመጠበቅ መውሰድ የምንችለው ርምጃ እንዳለ ግን እናውቃለን። በሁሉም የመንግስት እርከኖች በፓርቲዎች የጋራ ርምጃ እንዲህ ያለውን ነገር በጣም አልፎ አልፎ የሚገጥመን እንጂ ዘወትር የሚከሰት እንዳይሆን ማድረግ እንችላለን።” ሲሉ ፕሬዚደንቱ ኣሳስበዋል።

የትናንቱ ጥቃት በዩናይትድ ስቴትስት እ ኤ አ በ2012 ኣመተ ምህረት ከኔክቲከት ክፍለ ሀገር ሳንዲሁክ አንደኛ ደረጃ ትምህረት ቤት ሃያ ስድስት ሰዎች ከተገደሉበት ጥቃት ወዲህ ከደረሱት ሁሉ የከፋው ነው።

የቪኦኤው ሪቻርድ ግሪን (Richard Green) በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ እንዲህ ያለው የጅምላ ጥቃት ሲደርስ 355ኛ ጊዜ መሆኑን ገልጾ ያጠናቀረውን ቆንጂት ታዬ አቅርባዋለች። ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

ካሊፎርኒያ ሳን በርናርዲኖ ተኩስ ከፍተው አስራ አራት ሰው የገደሉት አጥቂዎች ማንነት ታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:08 0:00

XS
SM
MD
LG