በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካሊፎርኒያው ከባድ ዝናብና የደቀነው ሥጋት


"ይህ ሁኔታ ሲከሰት ወቅት የውሃውን መጠን ማጉደል የሚያስችል እርምጃ ወሰድን። በዚያም ጎርፉ በሚያደርሰው መሸርሸር ሳቢያ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ችለናል።” ቤል ክሮይል የካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የውሃ ሃብት መምሪያ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ናቸው።

“ይህ ሁኔታ ሲከሰት ወቅት የውሃውን መጠን ማጉደል የሚያስችል እርምጃ ወሰድን። በዚያም ጎርፉ በሚያደርሰው መሸርሸር ሳቢያ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ችለናል።” ቤል ክሮይል የካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የውሃ ሃብት መምሪያ ተጠባባቂ ዲሬክተር ናቸው።

ተጨማሪ ከባድ ዝናም እንደሚጥል እየተተነበየ ባለበት በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ ግድብ ጥሶ በመፍሰስ አካባቢውን እንዳያጥለቀልቅ የተሰጋውን ጎርፍ ለመቋቋም ጥድፊያ ተይዟል።

በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ በመጠኑ ግዙፉ መሆኑ በሚነገርለት ግድብ ያዘለውን ውሃ ከማጠራቀሚያ ለማፍሰስና ጉዳት የደረሰበትን መውረጃ ለመጠገን የምህንድስና ባለ ሞያዎች የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ላይ ናቸው።

በምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት ሰሞኑን የዘነመውን እጅግ ከፍተኛ ዝናም ተከትሎ የኦርቪልን ሃይቅ ግድብ ጥሶ በሚፈሰው ጎርፍ ሳቢያ በብዙ አሥርሺ የተቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች መኖሪያ ቀያቸውን ጥለው በመውጣት ወደ ጊዜያዊ መጠለያዎች ለመግባት ተገደዋል።

ዓመታት ከዘለቀ ድርቅ ገና የወጣችው የካሊፎርኒያ ግዛት ሪኮርድ ያስመዘገበ የክረምት ዝናም አስተናግዳለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የካሊፎርኒያው ከባድ ዝናምና የደቀነው ሥጋት
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:47 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG