በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡሩንዲ መንግስት የጦር መሣሪያ አሰሳ እያካሄደ ነው


በትናትናው እለት ታጣቂዎች ወደ ዘጠኝ የሚሆኑ ሰዎችን በብሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ መግደላቸው ተዘግቧል። ግድያውን ተከትሎ መንግስቱ ጦር መሣሪያ ያላስረከበሩትን ሰዎች ትጥቅ በማስፈታት ላይ ይገኛል።

የቡሩንዲ መንግሥት ቡጁምቡራ ከተማ ውስጥ ግድያዎች መፈጸማቸውን ተከትሎ፥ በተቃዋሚነት የሚጠረጠሩ ሰዎችን ትጥቅ ማስፈታት ቀጥሏል። የጦር መሣሪያ ያላስረከቡ ሰዎች እንደ ሀገር ጠላት ይቆጠራሉ ሲሉ ፕሬዘዳንቱ የሰጡት የጊዜ ገደብ ትላንት አብቅቷል።

ተንታኞችና የአሜሪካ መግሥት ሁኔታው አደገኛ ነው ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ዝርዝሩን ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የቡሩንዲ መንግስት የጦር መሣሪያ አሰሳ እያካሄደ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:43 0:00

XS
SM
MD
LG