በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካቫኖ ቃለ-መሃላ ፈፀሙ


በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሕንፃ ውስጥ የተከናወነውን የ114ኛውን የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ብሬት ካቫኖን ቃለ-መሃላ ሥርዓት የመሩት የፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ጃን ራበርትስ እና በጡረታ የተገለሉት አሁን ካቫኖ የሚተኳቸው አማካይ ድምፅ ሆነው ለረዥም ጊዜ እንዳገለገሉ የሚነገርላቸው አንተኒ ኬኔዲ ናቸው /ዋሺንግተን ዲ.ሲ. መስከረም 26/2011 ዓ.ም./
በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሕንፃ ውስጥ የተከናወነውን የ114ኛውን የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ብሬት ካቫኖን ቃለ-መሃላ ሥርዓት የመሩት የፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ጃን ራበርትስ እና በጡረታ የተገለሉት አሁን ካቫኖ የሚተኳቸው አማካይ ድምፅ ሆነው ለረዥም ጊዜ እንዳገለገሉ የሚነገርላቸው አንተኒ ኬኔዲ ናቸው /ዋሺንግተን ዲ.ሲ. መስከረም 26/2011 ዓ.ም./

ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛነት በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀረቡትን ብሬት ካቫኖን የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤቱ ቅዳሜ፤መስከረም 26/2011 ዓ.ም. ካፀደቀ በኋላ በግል በተከናወነ ሥነ-ሥርዓት ወዲያው ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል፡፡

ብሬት ካቫኖ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ እንዲሆኑ የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤቱ ከወሰነና ቃለ መሃላ ከፈፀሙ በኋላ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ የበረታ ቅሬታ እየተሰማ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀረቡትን ብሬት ካቫኖን ሹመት የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤቱ ያፀደቀው ትናንት (ቅዳሜ፤ መስከረም 26/2011 ዓ.ም.) ምሽት ላይ የነበረ ሲሆን ወዲያው በግል በተከናወነ ሥነ-ሥርዓት ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል፡፡

በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሕንፃ ውስጥ የተከናወነውን የ114ኛውን የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ብሬት ካቫኖን ቃለ-መሃላ ሥርዓት የመሩት የፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ጃን ራበርትስ እና በጡረታ የተገለሉት አሁን ካቫኖ የሚተኳቸው አማካይ ድምፅ ሆነው ለረዥም ጊዜ እንዳገለገሉ የሚነገርላቸው አንተኒ ኬኔዲ ናቸው፡፡

የሚስተር ካቫኖ ሹመት የፀደቀው ከምክር ቤቱ አባላት እንደራሴዎች የሃምሣውን ድምፅ በማግኘት ነው፡፡

የዳኛ ብሬት ካቫኖን ሹመት የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤቱ ያፀደቀው በምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ በተመራ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት ነበር
የዳኛ ብሬት ካቫኖን ሹመት የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤቱ ያፀደቀው በምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ በተመራ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት ነበር

ከሪፐብሊካኑ 49 ሴናተሮች የተቃወመ ማንም ካለመኖሩ በተጨማሪ ካቫኖ አንድ የዴሞክራት ሴናተር ተጨማሪ ድምፅ በማግኘታቸው ነው በሃምሣ ድጋፍና በ48 የዴሞክራቲክ ሴናተሮች ተቃውሞ ያለፉት፡፡

የአላስካ ሪፐብሊካን ሴናተር ሊሳ ሙርኮውስኪ በስብሰባው ላይ ቢገኙም ድምፃቸውን ሳይሰጡ ቀርተዋል። ለካቫኖ ሹመት የይሁንታ ድምፅ የሰጡት ዴሞክራት እንደራሴ የዌስት ቨርጂንያ ሴናተር ጆ ማንቺን ሳልሣዊ ናቸው።

በዚህ ዓይነት በታሪክ እጅግ ጠባብ በተባለ ልዩነት ሹመታቸው የፀደቀላቸው ካቫኖ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ 114ኛ ዳኛ ሆነዋል፡፡

በሚስተር ካቫኖ ሹመት ላይ የተሰጠው ድምፅ ሂደት ተጠናቅቆ ውጤቱ እንደተገለፀ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “እጅግ የሚያስፈነድቅ!” ባሉበት የትዊተር መልዕክት የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤቱን እንደሚያደንቁና “እንኳን ደስ አላችሁ” እንደሚሉ ገልፀው ተሰያሚውን ዳኛ “ታላቅ ተመራጭ” ሲሉ ጠርተዋቸዋል፡፡

ብሬት ካቫኖ
ብሬት ካቫኖ

ዋሺንግተን ዲ.ሲ. የሚገኘው ፌደራል ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ ሆነው የቆዩት ብሬት ካቫኖ “ከሰላሣ ዓመታት በፊት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳለን ሊደፍረኝ ሞክሮ ነበር” ባሉ ዶ/ር ክሪስቲን ብሌዚ ፎርድ የሚባሉ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ውንጀላ ምክንያት እንዲሁም ተከፋፍሎ የነበረው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ቆይቷል፡፡

ጉዳዩን ፌደራሉ የምርመራ ቢሮ እንዲያየው ተወስኖ ኤፍቢአይ ለሁለት ቀናት ያደረገውን ምርመራ ከትናንት በስተያ ሃሙስ ለሴኔቱ አቅርቧል፡፡

ኤፍቢአይ ያደረገው ምርመራ “በቂ አይደለም” በሚልና በዚሁ ክሥ ምክንያት ሚስተር ካቫኖ ለሴኔቱ እማኝነት በሰጡ ጊዜ “አንፀባርቀዋል” በተባለ “ወገንተኛ አስተያየት”ና “ግልፍተኛነት” ጭምር “ለታጩበት ከፍተኛ ወንበር ብቁ አይደሉም” የሚል የበረታ ተቃውሞ ከዴሞክራቶቹና ከሌሎችም ተሟጋቾች ሲነሣባቸው ሰንብቷል፡፡

የውሣኔ ድምፅ ለመስጠት ለከትናንት በስተያ ዓርብ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በዚሁ እሰጥ አገባ ምክንያት የድምፁን ጉዳይ ለትናንት ማሸጋገሩ ይታወሳል።

የዳኛ ብሬት ካቫኖ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መመረጥ ተቃዋሚዎች
የዳኛ ብሬት ካቫኖ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መመረጥ ተቃዋሚዎች

በሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ሊቀመንበርነት ድምፀ እየተሰጠ በነበረ ጊዜ በምክር ቤቱ የእንግዶች መቀመጫ ውስጥ የነበሩ ታዛቢዎች ያሰሟቸው በነበሩ “ቅሌ! ቅሌ!” በሚሉ የጩኸት ድምፆች ሂደቱ እየተቋረጠ ለመቀጠል ከመገደዱም በላይ ከውጭም ይስተጋቡ የነበሩ ተመሣሣይ የተቃዋሚ ሰልፈኞች ድምፆች አዳራሹን ዘልቀው ይሰሙ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዋይት ሃውስ ከገቡ ባለፉት ሃያ ወራት ውስጥ ዘጠኝ ዳኞች ለዕድሜ ልክ ለሚሰየሙበት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኛ ሹመት በተሣካ ሁኔታ ሲያስፀድቁ የዛሬው ሁለተኛቸው ሲሆን ካቫኖ ባላቸው አቋምና እምነት ምክንያት ወግ አጥባቂ ዘመም የሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማፅናት እንደቻሉ ይነገርላቸዋል፡፡

ለዳኛ ብሬት ካቫኖ የተሰጠ የሴናተሮች ድምፅ /ቀይ - ሪፐብሊካን፤ ሰማያዊ - ዴሞክራት/
ለዳኛ ብሬት ካቫኖ የተሰጠ የሴናተሮች ድምፅ /ቀይ - ሪፐብሊካን፤ ሰማያዊ - ዴሞክራት/

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ባወጡት የትዊተር መልዕክት “ለሰደድ ጫሪ ክብሪት እንዳይሰጡ ሁሉ ለግራ ዘመም ፖለቲከኞችም ሥልጣን አያጎናፅፉም” ሲሉ በውጤቱ የተሰማቸውን እርካታ አሳይተዋል።

ብሬት ካቫኖ የ53 ዓመት ዕድሜ ጎልማሣ ሲሆኑ ቢያንስ ለመጭዎቹ አርባ ዓመታት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛነት ሊያገለግሉ እንደሚችሉ ብዙዎች ተንብየዋል፡፡

ብሬት ካቫኖ ቃለ-መሃላ ፈፀሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG