በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብራዚል ፕሬዚዳንት “ከስልጣን እንዲወገዱ” የሚጠይቅ የክስ ሂደት በመከፈቱ ፕሬዚዳንቱ ምላሽ እንዲሰጡ እየተጠበቀ ነው

መንግስትን የሚደግፉ ተቃዋሚዎች የሕግ ምክር ቤት ምርጫ በቴሌቪዥን እየተከታተሉ /ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/
መንግስትን የሚደግፉ ተቃዋሚዎች የሕግ ምክር ቤት ምርጫ በቴሌቪዥን እየተከታተሉ /ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/

የብራዚል የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የ68 ዓመቱዋ ግራ ዘመም መሪ ከስልጣን እንዲሰናበቱ በመጪው ግንቦት ወር ድምጽ ሊሰጥ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፤ ይልቀቁ የሚል ውሳኔ ላይ ከተደረሰ የክስ ሂደቱ ባይጠናቀቅም ለስድስት ወር ያህል ስልጣን መልቀቅ ይኖርባቸዋል።

አራት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የኦሎምፒክ ውድድሮችን ዋና ከተማዋ ሪዮ ዲ ጃኒየሮ የምታስተናግደው ብራዚል፥ በፕሬዚዳንቱዋ ላይ “ከስልጣን እንዲወገዱ” የሚጠይቅ የክስ ሂደት መከፈቱን ተከትሎ የፖለቲካ ትርምስ ሰፍኖባታል። ፕሬዚዳንት ዲልማ ሩሴፍ ስለ ክሱ የሚሰጡት ምላሽ እየተጠበቀ ነው።

የኦሎምፒክ ውድድሮች እ.አ.አ. 2016 በዋና ከተማዋ ሪዮ ዲ ጃኒየሮ ይካሄዳል
የኦሎምፒክ ውድድሮች እ.አ.አ. 2016 በዋና ከተማዋ ሪዮ ዲ ጃኒየሮ ይካሄዳል

የብራዚል የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የ68 ዓመቱዋ ግራ ዘመም መሪ ከስልጣን እንዲሰናበቱ በመጪው ግንቦት ወር ድምጽ ሊሰጥ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፤ ይልቀቁ የሚል ውሳኔ ላይ ከተደረሰ የክስ ሂደቱ ባይጠናቀቅም ለስድስት ወር ያህል ስልጣን መልቀቅ ይኖርባቸዋል።

መወሰኛ ምክር ቤቱ የክስ ሂደቱ እንዲቀጥል ለመወሰን የሚያስፈልገው ቀላል አብላጫ ድምጽ ብቻ ነው። የብራዚል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሰማኒያ አንዱ የመወሰኛ ምክር አባላት አራባ አምስቱ ከስልጣን ማሰናበቻ ክስ ሂደቱ እንዲቀጥል ይደግፋሉ።

የብራዚልዋ ፕሬዚደንት ከታገዱ ባንድ ወቅት ደጋፊያቸው የነበሩት እና አሁን ግን ፕሬዚደንቱዋ ከሃዲ ብለው የሚወነጅሉዋቸው ምክትላቸው ሚሼል ቴሜር ስልጣኑን ይይዛሉ።

ዳሩ ግን እሳቸውም ቢሆኑ የመንግስት ንብረት ከሆነው ፔትሮባስ የነዳጅ ኩባኒያ ተፈጽሙዋል በተባለው ሙስና ጉዳይ ስማቸው ተነስቱዋል። ፕሬዚዳንት ሩሴፍ ላይ ለቀረው ክስ መነሾ የሆነውን የመንግስት በጀት የማምታታት ተግባር አንዳንዶቹ ላይ ምክትል ፕሬዚደንቱ ፈርመዋል ተብሏል።

የሀገሪቱ የህግ መምሪያው ምክር ቤት ትናንት ዕሁድ ባካሄደው ስድስት ሰዓት የፈጀና መጯጯህ የበዛበት የድምጽ አሰጣጥ ፕሬዚዳንቱዋን ማሰናበቻ ሂደት እንዲጀመር በከፍተና ድምጽ ብልጫ ወስኗል። ሌሊቱን ሳኦ ፖሎና ሪዮ ዲጃኒየሮ ርችት ሲተኮስ ያደረ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች የፕሬዚደንቱዋ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ሰልፍ ኣካሂደዋል።

ሩሴፍ በምክር ቤቱ ውሳኔ ላይ ወዲያውኑ አስተያየት አልሰጡም ዛሬ ማምሻውን ይናገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG