በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባና የባሕር ዳር እሥረኞቹ መለቀቅ


ሰማያዊ ፓርቲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ላለፈው አንድ ዓመት የሚሆን ጊዜ የመጀመሪያዊን ሕዝባዊ ስብሰባ ትናንት አዲስ አበባ ላይ አካሂዷል።

ሰማያዊ ፓርቲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ላለፈው አንድ ዓመት የሚሆን ጊዜ የመጀመሪያዊን ሕዝባዊ ስብሰባ ትናንት አዲስ አበባ ላይ አካሂዷል።

በመብራት ኃይል አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ቁጥሩ ከስምንት መቶ ያላነሰ ሰው መገኘቱን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታነህ ባልቻ ማምሻውን ለቪኤኤ ገልፀዋል።

የፊታችን ዕሁድ፣ መስከረም 26/2010 ዓ.ም ከምኒሊክ አደባባይ ተነስቶ መስቀል አደባባይ ላይ የሚጠናቀቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግም ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ሐሙስ፣ ጥቅምት 16/2010 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ባሕር ዳር ከተማ ላይ በነኀሴ 2ዐ1ዐ ዓ.ም. ተካሂዶ ከነበረውና ብዙ ጉዳይት ከደረበት ሰልፍ ጋር ተያይዞ በእሥር ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን፣ በተለይ ደግሞ የፓርቲውን የባሕር ዳር ከተማ መሪዎች በነፃ ማሰናበቱ ታውቋል።

በፓርቲው መሪዎችና አባላት ላይ ለአሥራ አንድ ወራት ያህል ክሥ ሳይመሠረት መቆየቱን ለቪኦኤ የገለፁት የፓርቲው የባሕር ዳር ከተማ ሰብሳቢ አቶ ማሩ ዳኘው እና ምክትላቸው አቶ መልከሙ ታደሰ ክሡ ሲቀርብም ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከዕድሜ ልክ እሥራት እስ ሞት የሚያሰቀጣ የወንጀል ክሥ እንደነበር አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባና የባሕር ዳር እሥረኞቹ መለቀቅ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:49 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG