ድሬዳዋ —
በአፋር ክልል ከትላንት 4 ሠዓት ጀምሮ የነበረው የመንገድ መዝጋት አድማ ማምሻውን እንደተጠናቀቀና መንገዶች እንደተከፈቱ ተገለፀ፡፡ ሶማሊ ነዋሪዎች የሚበዛባቸው ሶስት ቀበሌዎች ላይ እየተፈጠረ ያለውን ግጭት ለማርገብ በሚል ከቀበሌዎቹ የአፋር ክልል ልዩ ሃይል እንዲወጣ መደረጉን በመቃወም ነበር የክልሉ ወጣቶች ተቃውሞ የጀመሩት፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ተጓዦችንም ሆነ ንብረቶቻቸው ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያላደረሰ ነበር ተብሏል፡፡
ከአዋሽ ወደትግራይ የሚወስደው መንገድ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የተከፈተ ሲሆን ከመሃል አገር ወደምስራቅ ኢትዮጵያና ወደ ጂቡቲ የሚወስዱት መንገዶች ግን ማምሻውን 10፡35 ላይ ነው የተከፈቱት፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ