ዋሽንግተን ዲሲ —
ከ “ቢቂላ የሽልማት ድርጅት” ጋር በዛሬው ፕሮግራማችን እናስተዋውቃለን ። ኃላፊዎቹ ድርጀቱን የቢቂላ ሽልማት (Bikila Award Inc.) ይሉታል። ይህ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት፣ ፕሬዚደንቱ በቃለ-ምልልሱ እንደገለጹት፣ ሽልማት የሚገባቸውን መሸለም፣ እውቅና የሚገባቸውን ማስተዋወቅ ነው ዋና ትኩረቱ።
ሌላም ዓላማ ይኖረዋል። ለምኛውም የቢቂላ ሽልማት ድርጅት ፕሬዚደንትን አቶ ተሰማ ሙሉጌታን አነጋግረናል። የድርጅቱን ዓላማ ገልጸውልናል። ሙሉውን ዝርዝር የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ አዲሱ አበበ አቅርቦታል። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።