በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በዩናይትድ ስቴትስ የሚታየውን የሙቀት ማዕበል የተመለከቱ አዳዲስ ርምጃዎችን ይፋ አደረጉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጅግ ከፍተኛ የአየር ሙቀት በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች እየተዘገበ ባለበት ባሁኑ ወቅት የአየር ሁኔታ ትንበያዎችን ለማሻሻል፣ ለሠራተኞች መብት ጥበቃ መረጋገጥ እና የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የሚያግዙ አዳዲስ እርምጃዎችን ይፋ አደረጉ።

ፕሬዚዳንቱ የወጠኗቸው እነኚህ አዳዲስ እርምጃዎች ይፋ የተደረጉት፣ የብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት ቁጥራቸው 200 ሚሊዮን ለሚደርሱ አሜሪካውያን የከፍተኛ የአየር ሙቀት እና የጎርፍ ማስጠንቀቂያ በሰጠበት ወቅት ነው።

ባይደን ትናንት ኀሙስ ከዋይት ሐውስ ባሰሙት ንግግር፡ አሜሪካዊያን ለከፍተኛ የአየር ሙቀት እየተጋለጡ ባሉበት፣ “የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ ማንም ሊክድ አይችልም” ብለዋል።

“በቅድሚያም የሠራተኛ ጉዳይ ተጠባባቂ ሚኒስትር ጁሊ ሱ’ን የከፍተኛ ሙቀት አደጋ ማስጠንቀቂያ እንዲያውጁ ጠይቄያለሁ።”

"ዛሬ፣ ከፍተኛ የአየር ሙቀት በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶችና ከተሞች እያስከተለ ያለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም የሚያግዙ ተጨማሪ እርምጃዎችን እያስተዋወቅኩ ነው።” ብለዋል ባይደን፡፡

“በቅድሚያም የሠራተኛ ጉዳይ ተጠባባቂ ሚኒስትር ጁሊ ሱ’ን የከፍተኛ ሙቀት አደጋ ማስጠንቀቂያ እንዲያውጁ ጠይቄያለሁ።” ያሉት ባይደን፡ ደንቡ፣ ሠራተኞች ከከፍተኛ የአየር ሙቀት ጋር የተዛመደ በፌድራል ደረጃ ጥበቃ የሚደረግለት መብት እንዳላቸው የሚያብራራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

“ሠራተኞችን ከአደገኛ ሁኔታዎች መጠበቅ አለብን። ይህንንም እናደርጋለን።” በማለት እነዚህ ጥበቃዎች የማይደረጉባቸውን ግዛቶች እና ለሠራተኞች ጥበቃ አናደርግም የሚሉትን በስም እንደሚጠሩም ባይደን ተናግረዋል።

የሙቀት ወጀብ ክፍላተ ዓለምን እያዳረሰ ነው፤ ሀገራት ተጨባጭ ርምጃ እንዲወስዱ ፖፕ ፍራንሲስ በድጋሚ አሳሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በያዝነው የአውሮፓውያኑ የበጋ ወራት እየታየ ያለው እጅግ ከፍተኛ ሙቀት፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታየ ክስተት መሆኑንና “ያለንበት የሃምሌ ወርም በሞቃትነቱ በታሪክ እስከ ዛሬ ከተመዘገቡት ሁሉ ከፍተኛው ይሆናል” ሲሉ ሳይንቲስቶች ተናግረዋል።

የያዝነው ወር ከፍተኛ ሙቀት፣ ደቡብ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ‘ቃጠሎ’ ከሚሰኝ ደረጃ መድረሱ ተነግሯል፡፡ በፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት የውቅያኖስ ውሃ አንዳንዶች “የፈላ ገንዳ” ከሚሉት ደረጃ መድረሱም ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG