በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በካማሽ ዞን በሎ ጀገንፎይ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች "ድጋፉ በአግባቡ እየደረሰን አይደለም፤የድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ አባላት ለነጋዴዎች እየሸጡት ነው" ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።
የወረዳው አስተዳደርና ዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ተወካይ "ቅሬታው አሉባልታ ነው" በማለት ቢያስተባብሉም የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ በበሎ ጀገንፍይ ሶጌ ከተማ ተገኝተው ችግሩ እንዳለ መመልከታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ቅሬታውን በመመርመር መፍትሄ እንደሚሰጥ ገልጿል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።