በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት የሕይወት እና የንብረት ጉዳት መድረሱ ተገለጸ


በድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት የሕይወት እና የንብረት ጉዳት መድረሱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:37 0:00

በድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት የሕይወት እና የንብረት ጉዳት መድረሱ ተገለጸ

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ውስጥ፣ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት፣ አንድ ሰው መገደሉንና አምስት ሺሕ ያህል ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው መሰደዳቸውን ተጎጂዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

በወረዳው የቆርቄ ቀበሌ ጫካ ውስጥ የነበሩና የክልሉን መንግሥት የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከማኅበረሰቡ ጋራ የተቀላቀሉ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለው በዚኹ ጥቃት፣ 30 የሚደርሱ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች ተናግረዋል፡፡

የክልሉን መንግሥት የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከጫካ የገቡትና የቀድሞ የጉምዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር እና በአሁኑ ሰዓት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግራኝ ጉደታን፣ በታጣቂዎቻቸው ላይ ስለተነሣው ክስ ጠይቀናቸው፣ በጥቃቱ የታጣቂዎቻቸው እጅ እንደሌለበት ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG