በወረዳው የቆርቄ ቀበሌ ጫካ ውስጥ የነበሩና የክልሉን መንግሥት የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከማኅበረሰቡ ጋራ የተቀላቀሉ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለው በዚኹ ጥቃት፣ 30 የሚደርሱ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች ተናግረዋል፡፡
የክልሉን መንግሥት የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከጫካ የገቡትና የቀድሞ የጉምዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር እና በአሁኑ ሰዓት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግራኝ ጉደታን፣ በታጣቂዎቻቸው ላይ ስለተነሣው ክስ ጠይቀናቸው፣ በጥቃቱ የታጣቂዎቻቸው እጅ እንደሌለበት ተናግረዋል፡፡