በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ


የቤንሻጉል ጉምዝ ክልል
የቤንሻጉል ጉምዝ ክልል

ቤንሻጉል ጉምዝ ክልል፤ ጉባ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ የታጠቁ የአካባቢው ተወላጆች በአማራ ተወላጆች ላይ ከትናንት በስቲያ ፈፀሙት በተባለ ጥቃት አሥራ አራት ሲቪሎች መገደላቸውንናስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ጥቃቱ “የብሄር ማንነትን ለይቶ የተካሄደ ነው” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ።

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልአዚዝ መሀመድ ደግሞ “ጥቃቱ ብሄርን መሠረት ያደረገ አይደለም፤ የኅዳሴ ግድብ ውኃ ሙሌት መጠናቀቁን ተከትሎ ስኬቱን ለማደናቀፍ ተላላኪዎች የፈጠሩት ጥቃት ነው” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ በተፈፀም ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:23 0:00


XS
SM
MD
LG