ባህር ዳር —
ነፃነት ሥርዓተ አልበኝነትን፣ ሥርዓት አልበኝነት ደግሞ አምባገነንነትን ሊየመጣ እንደሚችል ሕብረተሰቡ እየተገነዘበ በመምጣቱ፣ የሕግ የበላይነት ይከበር ጥያቄ እያነሳ ነው ሲሉ የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ንግሡ ጥላሁን ገለፁ፡፡ በሌላም በኩል አርቲስት ታማኝ በየነ እና ሌሎች ታዋቂ የኪነጥበብ ባለሞያዎች በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ወደ ሀገሩ እንደሚገቡና በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ እንደሚኖር አቶ ንግሡ ጥላሁን ገልፀዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድና አብሮዋቸው ወደ አሜሪካ ተጉዞ የነበረው ቡድን አግኝቶ ከአነጋገሯቸው ታዋቂ ግለሰቦች መካከል አርቲስት ታማኝ በየነ አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡ የወቅቱን የክልሉን የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ