በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነሯ ስለ ትግራይ ስጋታቸውን ገለፁ


በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች
በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባከሌት፣ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች በከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ አስጠንቅቀዋል፡፡ በሰፊው እየተፈጸሙ መሆናቸው ከሚነገረው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መካከልም፣ አንዳንዶቹ የጦር ወንጀሎች ሊሆኑ እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡

በትግራይ እየተፈጸሙ ነው ፣ የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ በብዙ አካባቢዎች፣ የመገናኛ መስመሮች የተቋረጡ በመሆናቸው፣ ለማረጋገጥና መጠናቸውንም ለመግለጽ አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ባክሌት፣ ገለልተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብት አጣሪ ቡድኖች፣ በክልሉ ተዘዋውረው፣ ሁኔታዎችን ለመገምገም እንዲችሉና፣ እንዲሁም፣ ሰላማዊ ዜጎችን ከጥቃት ለመከላከልና፣ ወንጀል የፈጸሙትንም ለፍርድ ለማቅረብ እንዲቻል አካባቢው፣ ያለምንም ክልከላ ክፍት እንዲደረግም ጠይቀዋል፡፡

የኮሚሽነሯ ቃል አቀባይ፣ ሊዝ ትሮሴል እንደሚሉት፣ በአካባቢው የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብትና ህጎችን የጣሱ ድርጊቶች፣ በሁሉም ወገኖች እየተፈጸሙ መሆኑን፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ቢሮ፣ በየጊዜው ሪፖርት እንደሚደርሰው ተናግረዋል፡፡ ስለሪፖርቶቹም ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ

እነዚህ ሰላማዊ ዜጎች የሚዙባቸው አካባቢዎችን በከባድ መሳሪያዎች መደብደብን፣ ሰላማዊ ዜጎችን ሆን ብሎ ማጥቃትን፣ በዘፈቀደ የሚካሄዱ ግድያዎችና በስፋት የሚካሄዱ ዝርፊያዎችን ያጠቃልላሉ፡፡

የዓይን እማኞች እንደገለጹት በኤርትራ አዋሳኝ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው የሁመራ ከተማ፣ ከኖቬምበር 9 እስከ 11 ባሉት ቀናት የከባድ መሳሪያ ድብደባ መፈጸሙን አስታውቀዋል፡፡ ከኤርትራ የተተኮሱ በርካታ የከባድ መሳሪያ ጥይቶች የመኖሪያ ቤትና ሆስፒታሎችን ስለሞታቸው በርካታ የከተማይቱን ነዋሪዎች አነጋግረናል፡፡

የኢትዮጵያ ወታደሮች እና የአማራ ታጣቂዎች ሚሊሻዎች፣ ሁመራን መቆጣጠራቸውን ትሮሴል ተናግረዋል፡፡ ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸውን፣ በሆስፒታል፣ ባንኮች የንግድ ድርጅቶች፣ ገበያዎችና የግል መኖሪያ ቤቶች ላይ፣ ዘረፋዎች ተፈጽመዋል የሚል ክስ መቅረቡንም ገልጸዋል፡፡

ትሮሴል በከተማ ውስጥ ተፈጽመዋል ብለው ከዘረዘሯቸው አስደንጋጭ አደጋዎች መካከል፣ እጅግ የከፋውና፣ ብዙ መቶዎች፣ በዋናነትም የአማራ ተወላጆች የተገደሉበትን፣ የኖቬምበር 9ን እልቂት በማንሳት የሚከተለውን ብለዋል፡፡

“ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ቀደም ሲል አበክረው እንደተናገሩት፣ በአንድ ወገንም ይሁን የግጭቱ ተካፋይ በሆኑት ሁሉም ወገኖች ይሁን፣ በተፈጸመው ጥቃት፣ ሰላማዊ ዜጎች ሆኖ ተብለው ተገድለዋል፡፡ እነዚህ ግድያዎች ወደ ጦር ወንጀልነት ሊያድጉ ይችላሉ፡፡ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥና ፍትህን ለማስፈን ገለልተኛ፣ ነጻ፣ ግልጽና ጥልቅ የሆነ ምርምራ ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡”

የኮሚሽነሯ ቃል አቀባይ ትሮሴል፣ የኤርትራ ወታደሮች፣ ትግራይ ውስጥ መታየታቸው፣ ተፈጽመዋል በተባሉት፣ የጥላቻ ጥቃቶች፣ ከዚያም ጋር በተያያዘው ፣ የዓለም አቀፍ ህግ ጥሰቶች ውስጥ መሳተፋቸውን አስመልክቶ፣ ገና በሚገባ ያልተረጋገጠ ቢሆንም፣ መረጃዎች ወደ ድርጅቱ ቢሮ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፣ የኤርትራው ወታደሮች በግጭቱ ተሳታፊ መሆናቸውን አስተባብሏል፡፡

ግጭቱ ከመጀመሩ ሰባት ሳምንታት በፊት፣ 96 ሺ የሚሆኑ ኤርትራውያን ስደተኞች፣ በትግራይ በሚገኙት የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ተጥልለው ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ፣ ብዙዎቹ ለደህንነታቸው በመስጋት፣ መጠለያ ካምፖቹን ትተው ሸሽተዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ ፊሊፖ ግራንዲ እንደተናገሩት፣ በትግራይ የሚገኙ በርካታዎቹ ስደተኞች፣ የተገደሉ፣ የታፈኑ እና በግዴታ ተይዘው ወደ ኤርትራ የተመለሱ መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት፣ ከወኪሎቻቸው የደረሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጠቀሰው ጊዜ አካባቢም፣ ዩናይትድ ስቴትስ ፣የኤትርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መገኘታቸውን በመግልጽ ለቀው እንዲወጡ ጥሪ ማስተላለፏም ይታወቃል፡፡ (ዘገባው የቪኦኤ ዘጋቢ ሊሳ ሽላይን ነው፡፡)

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነሯ ስለ ትግራይ ስጋታቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:04 0:00


XS
SM
MD
LG