በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካዛክስታን ውስጥ የተከሰከሰው አውሮፕላን አደጋ መንስዔ በማጨቃጨቅ ላይ ነው


ካዛክስታን ውስጥ የተከሰከሰው አውሮፕላን
ካዛክስታን ውስጥ የተከሰከሰው አውሮፕላን

ካዛክስታን ውስጥ የተከሰከሰውና 38 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡበትን የአውሮፕላን አደጋ መንስኤ በተመለከተ ሩሲያ እና ሌሎች ወገኖች ጣት በመጠቋቆም ላይ ናቸው። በአደጋው 29 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ስድሳ ሰባት መንገደኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረው የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን ካዛክስታን ውስጥ በተከሰከሰበት ወቅት በቼችንያ ክልል ውስጥ በዩክሬን የድሮን ጥቃት በመፈጸም ላይ እንደነበር የሩሲያ ሲቪል አቪዬሽን ኅላፊ ዲሚትሪ ያድሮቭ ሲናገሩ፣ አንድ የአዘርባይጃን ምክር ቤት አባል እና በርካታ የአቪዬሽን ባለሙያዎች ደግሞ አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሩሲያ በተተኮሰ የአየር መቃወሚያ መሆኑን ይገልጻሉ።

አውሮፕላኑ ከአዘርባጃን መዲና ባኩ ወደ ሩሲያዋ የቼችንያ መዲና ግሮዝኒ በማምራት ላይ እንደነበር ታውቋል። አውሮፕላኑ አቅጣጫውን በመቀየር በካዛክስታኗ አክታ ከተማ በድንገት ለማረፍ በመሞከር ላይ ሳለ ተከስክሷል።

የአዘርባጃን፣ ካዛክስታን እና የሩሲያ ባለሥልጣናት የአደጋውን መንስኤ በተመለከተ ከመናገር ተቆጥበው የነበረ ቢሆንም፣ ራሲም ሙሳቤኮቭ የተባሉ የአዘርባጃን ምክር ቤት አባል፣ አውሮፕላኑ በግሮዝኒ ሰማይ ላይ ሳለ ተመትቶ እንደወደቀ ለሃገሪቱ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። “ሩሲያ ይቅርታ ትጠይቅ” ሲሉም አክለዋል።

የፓርላማ አባሉን መግለጫ በተመለከተ የተጠየቁት የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፣ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበው፣ "የአደጋውን መንስኤ የሚወስኑት መርማሪዎች ናቸው" ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG