በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን ተከስክሶ 38 ሞቱ


ዛኪስታን ውስጥ የተከሰከሰው የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን፤ በክልሉ አስተዳደር ከተለቀቀው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል፤ በአክታዉ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ፣ ካዛክስታን፣ እአአ ታኅሣሥ 25/2024
ዛኪስታን ውስጥ የተከሰከሰው የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን፤ በክልሉ አስተዳደር ከተለቀቀው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል፤ በአክታዉ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ፣ ካዛክስታን፣ እአአ ታኅሣሥ 25/2024

ስድሳ ሰባት መንገደኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አንድ የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን ካዛኪስታን ውስጥ ተከስክሶ 38 ሰዎች ሲሞቱ 29 የሚሆኑት ተርፈዋል።

አውሮፕላኑ ከአዘርባጃን መዲና ባኩ ወደ ሩሲያ ግሮዝኒ ከተማ በማምራት ላይ እንደነበር ታውቋል። አውሮፕላኑ አቅጣጫውን በመቀየር በካዛኪስታኗ አክታ ከተማ በድንገት ለማረፍ በመሞከር ላይ ነበር።

የአዘርባጃኑ ፕሬዝደንት ኢልሃም አሊየቭ የአደጋውን ምክንያት ከወዲሁ ለመናገር ባይቻልም፣ በነበረው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ለመቀየር ተገዶ ነበር ብለዋል።

የሩሲያው ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በበኩሉ፣ ቀድመው የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አውሮፕላኑ ከወፎች ጋራ በመጋጨቱ ችግሩ ሊፈጠር ችሏል ብሏል።

በአውሮፕላኑ ውስጥ 42 የአዘርባጃን ዜጎች፣ 16 ሩሲያውያን፣ ስድስት ካዛክስታናውያንና ሶስት ኪርጊስታናውያን እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG