በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር የአገራቸውን እና የኬንያን የመከላከያ ኃይሎች ትስስር አወደሱ


የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን በዛሬው ዕለት ማንዳ ቤይ - ኬንያ በሚገኘው ሲምባ የጦር ካምፕ ተገኝተው የሁለቱን ሃገሮች ወታደሮች በጎበኙበት ወቃት በሰጡት አስተያየት በዩናይትድ ስቴትስ እና በኬንያ ኃይሎች መካከል ያለውን ግንኙነት "ጠንካራ" ሲሉ አወድሰዋል።

"በጋራ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ማድረግ የሚያስችል መግባባት ምሳሌ ናችሁ" ያሏቸው ኦስቲን አክለውም፤ "አንዳንድ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ጉዳዮችን ጨምሮ በመተባበር እና በመደጋገፍ በየዕለቱም በጋራ በመስራት ላይ ናችሁ" ሲሉ የሁለቱን አገሮች ሰራዊት አድንቀዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኬንያ በምስራቅ አፍሪቃ የጸረ ሽብር ጥረቶችን ለማጠናከር እና የኬንያ ኃይሎች በሄይቲ የሚሰማራውን የጸጥታ አስከባሪ ተልዕኮ ለመምራት የያዙትን ጥረት ለመደገፍ የሚያስችል

የአምስት አመት የመከላከያ ስምምነት በትላንትናው ዕለት ተፈራርመዋል።

ኬንያ በአካባቢው እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ላደረገችው የመሪነት ሚና ዩናይትድ ስቴትስ አመስጋኝ ናት"

"ኬንያ በአካባቢው እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ላደረገችው የመሪነት ሚና ዩናይትድ ስቴትስ አመስጋኝ ናት" ያሉት ኦስቲን፤ ሄይቲ ውስጥ በወረበላ ቡድኖች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመዋጋት ከዓለም ዙሪያ የተውጣጣውን ሕብረ-ብሄራዊ የጸጥታ ኃይል ለመምራት ፈቃደኛ በመሆኗም ምስጋና አቅርበዋል።

የባደን አስተዳደር ለሄይቲ ተልዕኮ የሚውል የ100 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለመመደብ ባለፈው ሳምንት ከመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደ ውይይት ወቅት ቃል በገባው መሠረት፡ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ይሰራል ብለዋል። ኦስቲን አያይዘውም፡ ለሄይቲ ለታቀደው ሕብረ-ብሄራዊ የደህንነት ተልዕኮ ሌሎች ሃገሮችም የኬንያን አርአያነት እንዲከተሉና ተጨማሪ የሰው ኃይል፣ ቁሳቁስ፣ ስልጠና እና እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ኬንያ የሄይቲው ፕሬዝዳንት ጆቭኔል ሞይስ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በሃምሌ 2021 ከተገደሉ በኋላ ተባብሶ የቀጠለውን የወሮበሎች ጥቃት ለመከላከል የሚግዝ 1,000 አባላት ያሉት የጸጥታ ኃይል ወደ ሄይቲ ለመላክ ቃል ገብታለች። በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት መጽደቅ የሚጠበቅበት የፀጥታ አስከባሪ ተልዕኮ ባለፈው ጥቅምት ወር የሄይቲው ጠቅላይ ሚንስትር አሪኤል ሄንሪ ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ የተወጠነ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG