ዋሺንግተን፤ ዲሲ / ለንደን —
“በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተቆጡ ብረትና ተቀጣጣይ ነገሮችን የያዙ” ያሏቸው ሃምሳ የሚሆኑ ወጣቶች ኤምባሲውን መውረራቸውን፣ የሃገሪቱን ባንዲራ አውርደው ሌላ ባንዲራ መስቀላቸውን፣ ሲወጣ ያገኙትን አንድ ተገልጋይ መደብደባቸውን፣ በሩን በኃይል ጥሰው ለመግባትና ጉዳት ለማድረስ መሞከራቸውን፣ መስኮት መስበራቸውን ገልፀዋል።
አምባሳደሩ ፖሊስ መጥራታቸውንና ለእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ደውለው የጥበቃና የፀጥታ ድጋፍ መጠየቃቸውንና በሥፍራው የተገኙት የፖሊስ አባላት አስፈላጊ ናቸው የሚሏቸውን መረጃዎች መሰብሰባቸውን ተናግረዋል።
መሉውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።