በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤይሩት ወደብ በደረሰው ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ


ሊባኖስ ቤይሩት ወደብ ላይ በደረሰው ግዙፍ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 137 ከፍ ብሏል። በፍንዳታው የቆሰሉት ደግሞ ከ5ሽህማለፋቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። የአደጋው ሰለባዎችን ከፍርስራሾች ውስጥ ለማውጣት የተሰማሩ ሰራተኞች ፍለጋዎቻቸውን ቀጥለዋል።ወዴት እንደገቡ ያልታወቀ፣ ያልተገኙ እንዳሉ ተገልጾ የሟቾቹ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ አይቀርም ተብሏል።

የቀድሞዋ የሊባኖስ ቅኝ ገዥ የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ በቤሩት ጉብኝት አድርገዋል፤ ያች ሃገር ጠንከር ያሉ የለውጥ እርምጃዎችን ካልወሰደች ይዞታዋ እያሽቆለቆለ መሄዱን መቀጠሉ የማይቀር ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከሀገሪሩ የፖለቲካና የተቋማት መሪዎች ጋር ሁኔታውን ፍርጥርጥ አድርገን ተወያይተንበታል ብለዋል ማክሮን።

ፈረንሳይ ወደሊባኖስ የአጣዳፊ ህክምና ዶክተሮችንና ብዙ ቶን የህክምና መሳሪያዎችና ቁሳቁስ በመላክ ላይ መሆንዋ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG