በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤይሩት ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ከ1መቶ ማለፉንና ከ4ሺህ በላይ መቁሰላቸው ተገለፀ


ትናንት ሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ወደቡ ላይ በደረሰ ከባድ ፍንዳታ ቢያንስ የ1መቶ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ ከ4ሺህ በላይ መቁሰላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

አንድ የቀይ መስቀል ባለሥልጣን እጅግ የከበደ መቅሰፍት ሲሉ በገለፁት በዚህ ፍንዳታ ወደቡ በአብዛኛው ወድሟል፤ በከተማዋ ያሉ ህንፃዎችና የቆሙ መኪናዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ደም በደም የሆኑ እና ድንጋጤ የዋጣቸው ቁስለኞች የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ሲንቆራጠጡ በቴሌቭዥን ዘገባዎች ታይተዋል።

የፍንዳታው መነሾ ምን እንደሆን በውል ያልታወቀ መሆኑን ሲገለፅ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ወደቡ ላይ መጋዘን ውስጥ የተከማቸ ለፍንዳታ አደጋ ተገላጭ የሆነ ሶዲየም ናይትሬት ሳይሆን አይቀርም ብለው መጠርጠራቸውን አንድ የሀገሪቱ ቴሌቭዥን ዘግቧል።

ነዋሪዎች ከፍንዳታው ቦታ ብርቱካንማ ቀለም ያለው ጢስ ወደሰማይ ሲንቦለቦል አይተናል ያሉ ሲሆን ከናይትሬት ጋር የሚያያዝ መሆኑን ይናገራሉ።

የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብ ብሄራዊ የሃዘን ቀን ሆኖ አውጀዋል።

XS
SM
MD
LG