በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ ኃይለኛ ዝናብ ባስከተለው የግድብ መደርመስ ከ47 በላይ ሰዎች ሕይወት ጠፋ

በኬንያ ኃይለኛ ዝናብ ባስከተለው የግድብ መደርመስ ቢያንስ ከ47 በላይ ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ፣ የንግድ መደብሮችን ጠራርጎ ወስዷል። ከናይሮቢ ሰሜን ምዕራብ 150 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሶላይ ከተማ በደረሰው አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡

በኬንያ ኃይለኛ ዝናብ ባስከተለው የግድብ መደርመስ ቢያንስ ከ47 በላይ ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ፣ የንግድ መደብሮችን ጠራርጎ ወስዷል። ከናይሮቢ ሰሜን ምዕራብ 150 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሶላይ ከተማ በደረሰው አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡

በአደጋው የሰው ሕይወት መጥፋት፣ የመብራት ኃይል መቋረጥ፣ የቤቶች ውድመት ጉዳት በተጨማሪ አርባ የሚሆኑ ስዎች ተርፈው ሆስፒታል እንደተወሰዱ የመድኅን ሰራተኞች ሰዎችን ለማዳን ገና እየፈለጉ መሆናቸውን ባለሥልጣኖች ገልፀዋል።

አከባቢው ካልፉት ሁለት ወራት ወዲህ ከባድ ዝናብ ሲዘንብ ቆይቷል። በጎርፍ መጥለቅለቅና በአፈር መደርመስ ምክንያት ከ130 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በወረደው ከባድ ዝናብ ምክንያት 220,000 የሚሆኑ ሰዎች ከመኖርያቸው መፈናቀላቸውን የኬንያ መንግሥት ትላንት ተናግሯል።

በኬንያ ኃይለኛ ዝናብ ባስከተለው የግድብ መደርመስ ከ47 በላይ ሰዎች ሕይወት ጠፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:32 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG