ዋሺንግተን ዲሲ —
1ሺሕ 438ኛው የኢድ-አለድሃ በዓል ዛሬ በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በዓሉ በኢትዮጵያም በፀሎትና በሶላት ሥነ ሥርዓት ተከብሯል።
እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ዋሺንግተንና አካባቢዋ የሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮችም ዛሬ ጠዋት በታላቁ መስጊድ በዓሉን አክብረዋል።
ለሶላት እንደተሰባሰቡም የፈርስት ሂጂራ የኢትዮጵያ ማኅበረሠብ ኢማም - ሼህ ኻሊድ መሐመድ ዑመር ቡራኬ ሰጥተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ